Addis Zemen (Nov 03, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 002/2019
በወሎ ዩኒቨርሲቲ የላኮመንዛ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ስር በደሴ እና ኮምቦልቻ ለሚገኙት መድኃኒት ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የሰው መድኃኒቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ፡–
1. ተጫራቾች፤– የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በዘርፉ አግባብ ያለውና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን፤ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ተያያዥ ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በኢትዮጵያ በታወቀ ባንክ የተመሰከረለት ለእያንዳንዳቸው መድኃነት ቤት የብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ) CPO በድርጅቱ ትክክለኛ ስም ላኮመንዛ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መግዣ ለእያንዳንዳቸው መድኃነት ቤት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከኢንተርፕራይዙ አስ ፋይ አገ ዘርፍ ግዥ ቡድን ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
4. ጨረታውን የሚያቀርበውና የሚፈርመው ወኪል ከሆነ ከሚመለከተው ውክልና ሰጭ (መዝጋቢ አካል) የተሰጠ ህጋዊ የውክልና ማስርጃ ማቅረብ ይኖርበታል።
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በመሙላት ዋናና አንድ ኮፒ በታሸገ ፖስታ የተጫራቹ ድርጅት ማኅተም ተደርጎበትና ተፈርሞ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ ብሎክ 20 ቢሮ ቁጥር 2023 በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ አስፋይ አገ /ዘርፍ ግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሰከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት አለባቸው።
6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተራ ቁጥር 5 በተጠቀሰው ቀን እና ቢሮ ከጧቱ 4፡30 በግልፅ ይከፈታል፤ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
7. ተጫራቾች ባይገኙም ሰነዳቸው የተሟላ ሆኖ ከተገኘ በሌሉበት የሚከፈት ይሆናል።
8. ከተጠቀሰው ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ የመወዳደሪያ ሀሳብ ወይም ጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
9.ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ያሸነፉትን ዕቃ በደሴ እና ኮምቦልቻ የኢንተርፕራይዙ ንብረት ክፍል የሚገኝበት ቦታ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
9. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% በኢትዮጵያ በታወቀ ባንክ የተመሰከረለት CPO ውል ማስከበሪያ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
10.አሸናፊ ተጫራች በውሉ ውስጥ የተካተቱትን ህጐች ማክበር አለባቸው።
11.ኢንተርፕራይዙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ማሳሰቢያ፡_ የጨረታ ሰነድ ሲያስገቡ ለየትኛው መድኃኒት ቤት ማለትም ለደሴ ወይም ለኮምቦልቻ መሆኑን በሰነዱ ማሸጊያ ላይ መግለጽ ይጠበቅባችኋል።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09212659119/0910449497 መጠቀም ይችላሉ
ላኮመንዛ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ