Be'kur (Nov 02, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን በሊቦ ከምከም ወረዳ የአዲስ ዘመን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
- ሎት1. የጽ/መሳሪያ፣
- ሎት 2. የጽዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 3. ሌሎች አላቂ ዕቃዎች (የመብራት አምፖል ሎት 3.1. የውሀ እቃዎች፣
- ሎት 4. የህትመት አገልግሎት ግዥ አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ ከአቅራቢዎች መካከል አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ተመዝጋቢ የሆኑ ፡፡
- የግዥ መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ለሆኑ ግዥዎች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ
መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ - ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ
ኦርጅናል ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ - የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ እያንዳንዱን ሎቶች ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 9 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የዕቃውን (አገልግሎት) ግዥ የተጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ኮፒውን ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአ/ዘመን መ/ደ/ሆስፒታል በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡ/መሪ ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት (በሌሉበት) በሆስፒታሉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 01 በ11ኛው ቀን በ3:15 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ (በከፊልም) የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ በህግ የተከለከለ ነው፡፡መ/ቤቱ በጨረታ ዋጋ መጠን ላይ እስከ 20 በመቶ የመቀነስና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 444 03 71 /09 18 02 46 84 /09 18 61 70 63 /09 49 65 55 86 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአዲስ ዘመን መጀመሪያ ደረጃ
ሆስፒታል