Be'kur (Nov 02, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የጉና በጌምድር ወረዳ ገንዘብ ኢ/ል/ጽ/ቤት ለጉና በጌምድር ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2. የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 3. የመኪና ጎማ እና ባትሪ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ወይም የሥራ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) እንዲሁም የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. ግዥው ከብር 500,00 (አምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1. ብር 13,000፣ ለሎት 2. ብር 7,000 ብር፣ ለሎት 3. ብር 10,000 በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በማስያዝ መረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሽገ ፖስታ ውስጥ አድርጎ በጉና በጌምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 17 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
7. ጨረታው የሚቆየው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን ሲሆን በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡
8. የዋጋ ዝርዝር መግለጫውን ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኝ ሲሆን በሚሞሉበት ሰዓት ሥርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ መነካካት እና ሁለት አይነት ዋጋ ማስቀመጥ የለባቸውም፡፡
9. የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
10. አሸናፊው የሚለየው በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በዋጋ መሙያ መሰረት በሎት በጠቅላላ ድምር ብቻ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አሸናፊነቱን እንደተገለፀለት በ5 ተከታታይ ቀን ውስጥ ያሸነፉበት 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ውል መውሰድ ያለበት ሲሆን በወቅቱ ቀርቦ ውል መውሰድ ካልቻለ በግዥ መመሪያው 144/2018 መሰረት አስፈላጊውን እርምጃ የምንወስድ ይሆናል፡፡
11. መ/ቤቱ 20 በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ሳንፕል የተቀመጡ እቃዎችን ቸክ አድርጋችሁ እንድትሞሉ እንዲሁም እቃዎቹን በ10 ቀን ውስጥ ማስረከብ አለባችሁ፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 251 02 26 ደውለው አስፈላጊውን መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጉና በጌምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት