የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የዞኑ ጤና መምሪያ ለሚያስገነባው ለጌሜዶ ጤና ጣቢያ ቀሪ ስራዎች ግንባታ የሥራ ተቋራጮችን (BC-7/GC-7 እና ከዚያ በላይ) አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የዞኑ ጤና መምሪያ ለሚያስገነባው ለጌሜዶ ጤና ጣቢያ ቀሪ ስራዎች ግንባታ የሥራ ተቋራጮችን (BC-7/GC-7 እና ከዚያ በላይ) አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 02, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የዞኑ ጤና መምሪያ ለሚያስገነባው ለጌሜዶ ጤና ጣቢያ ቀሪ ስራዎች ግንባታ የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፦ 

1. ደረጃቸው BC-7/GC-7 እና ከዚያ በላይ የሆነ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራከሽን ሚኒስቴር ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል የጨረታ ሰነዱን ከሀዲያ ዞን ፋይናንስ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 25ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ባለፊቃዱ ወይም ሕጋዊ ተወካዩ አንድ ኮፒ የሰነድ ማስረጃ በማስያዝ መግዛት ይችላል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስም 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያሰተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bank guarantee letter/ ከፋይናንሻል ሰነድ ጋር በፖስታ በሰም አሽገውና ማህተም በማድረግ ፈርመው ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች አስፈላጊውን ዕቃና ሠራተኛ አቀርበው ሥራውን የሚሠሩበትን የፋይናንሻል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም አራቱንም ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጐና የፕሮጀክቱን ስም ጠቅሶ የቴክኒካል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ ሰነዶች እንዲሁም ኦርጂናል ቴክኒካል ሀሳብ የያዘ ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ አራቱንም የቴክኒካል ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጎና ሁለቱንም የቴከኒካ እንዲሁም የፋይናንሻል ፖስታዎች በአንድ ማጠቃለያ እናት ፖስታ በማድረግ የፕሮጀክቱን ስም ጠቀሶ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጅ ሣጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 26ኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶች ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጭ ያደርጋል። የአገለግሎት ዋጋው በሰነዱ ላይ በተዘጋጀው ቦታ በአሃዝና በፊደል መሞላት ይኖርባቸዋል። ኦርጅናል የቴክኒካል ሃሣብ የያዘ ሰነድ (Bidder Certification of Complarce) በየመጠይቁ (ባዶ ቦታዎች ተሞልቶ ተፈርሞና መሃተም ተደርጎ ታሽጐ መመለስ አለበት። የቴክኒካል ሃሣብ የያዘውን ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) አለመመለስ ከውድድር ውጭ ያደርጋል።

4. ጨረታው በ26ኛው ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሀዲያ ዞን ፋይናንስ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፣ 26ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

ማሳሰበያ፡–

  • የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የመንግስት የግዢ አፈፃጸም መመሪያ ተፈጻሚ ይሆናል።
  • ማንኛውም ተጫራች ከወቅቱ ገበያ ዋጋ በታቸ ያቀረበ እንደሆነ ለሰሪው መ/ቤት ውል ለመግባት አይገደድም።
  • ማንኛውም ተጫራች በመንግስት ኤሌክትሮኒክስ ግዢ (EGP) የተመዘገበ መሆን አለበት።

 ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር

የሆሳዕና ዞን ፋይናንስ መምሪያ

ሆሳዕና


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *