የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት ለኮሚሽኑ ስራዎች የሚያስፈልጉ የተለያዩ አይነት ዕቃዎችን የፅ/መሳሪያ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የህክምና ዕቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት ለኮሚሽኑ ስራዎች የሚያስፈልጉ የተለያዩ አይነት ዕቃዎችን የፅ/መሳሪያ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የህክምና ዕቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 02, 2026)

የተለያዩ አይነት ዕቃዎች ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ ማስታወቂያ ቁጥር (ሁለት) 02/ 2019 ዓ.ም

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት ለኮሚሽኑ ስራዎች የሚያስፈልጉ የተለያዩ አይነት ዕቃዎችን የፅ/መሳሪያ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የህክምና ዕቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች –

1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው!

  • የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
  • በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው
  • የአቅራቢነት ምስከር ወረቀት ያለው
  • የታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምሥከር ወረቀትና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ሰርቲፍኬት ያለው
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/Bid Bond/ለሚያቀርቡት የዕቃ ዋጋ

  • የተሞላው ዋጋ ከብር 50,001.00 እስከ 500,000.00 ከሆነ የብር 5,000.00 በባንክ የተመሠከረለት ቼክ /CPO/ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • የተሞላው ዋጋ ከብር 500,001.00 እስከ 1,000,000.00 ከሆነ የብር 10,000.00 በባንክ የተመሠከረለት ቼክ /CPO/ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • የተሞላው ዋጋ ከብር 1,000,001.00 እስከ 5,000,000.00 ከሆነ የብር 50,000.00 በባንክ የተመሠከረለት ቼክ /CPO/ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • የተሞላው ዋጋ ከብር 5,000,001.00 በላይ ከሆነ የብር 200,000.00 በባንክ የተመሠከረለት ቼክ /CPO/ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች አንድ ተጫራች የሰጠውን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው የተሞላው ዋጋ ከዘጠና ቀናት (90) በታች መሆን የለበትም፡፡

4. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

5. የቴክኒካል ስፔስፍኬሽን እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በቅጂ ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በጨረታ ሰነድ ላይ በተጠቀሰው መሠረት በግልጽ ማቅረብ አለባቸው፡፡

8. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15ኛው ቀን በኋላ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከቀኑ 08፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ጨረታውም በዚሁ ዕለት ከሰዓት በኋላ 08፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሚሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

9. ኮሚሽኑ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል በሚዋዋልበት ጊዜ 20% የመጨመር ወይንም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

10. ኮሚሽኑ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል ከተዋዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ወር ባለው ጊዜ ውስጥ 25% የመጨመር መብት አለው፤

11. ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ሞባይል ቁጥር 0910 062 954 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን