የምሥራቅ ጎጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በእነማይ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሥር ለሚገኘው የወቀር አነስተኛ ወንዝ ጠለፋ የመስኖ ፕሮጀክት ግንባታ (ሎት 1) እና ለእነማይ ወረዳ ውኃ እና ኢነርጂ ልማት ጽ/ቤት የውሃ ክሎሪን እና እቃዎች ግዥ (ሎት 2) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የምሥራቅ ጎጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በእነማይ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሥር ለሚገኘው የወቀር አነስተኛ ወንዝ ጠለፋ የመስኖ ፕሮጀክት ግንባታ (ሎት 1) እና ለእነማይ ወረዳ ውኃ እና ኢነርጂ ልማት ጽ/ቤት የውሃ ክሎሪን እና እቃዎች ግዥ (ሎት 2) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Nov 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በምሥራቅ ጎጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የግዥ ንብ/አስ/ቡድን በእነማይ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሥር ለሚገኘው በክልል በጀት ለሚገነባው

  • ሎት 1. የወቀር አነስተኛ ወንዝ ጠለፋ የመስኖ ፕሮጀክት ግንባታ እንዲሁም
  • ሎት 2. ለእነማይ ወረዳ ውኃ እና ኢነርጅ ልማት ጽ/ቤት የውሃ ክሎሪን እና እቃዎች ግዥ በመደበኛ በጀት የግንባታ ሥራውን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን በመጋበዝ ለማሰራት ማንኛውንም የሚያሰወጣ ማቴሪያልም ሆነ የሰው ሀይል ተጫራቹ ራሱ ችሎ ማስራት እና መግዛት ይፈልጋል፡፡
  1. ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የቫት ሰርተፊኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ከገቢዎች ጽ/ቤት ማስያዝ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. ለሎት 2. የግዥ መጠኑ ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ ለሎት 1. በዘርፉ አግባብነት ያለው 2 አመት እና በላይ የስራ ል ምድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ማንኛውም ተቋራጭ በደረጃ WWC 5 እና ከዚያ በላይ የሆነ የታደሰ የውሃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ከጨረታው አሸናፊ ላይ 3 በመቶ ታክስ የሚቆረጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1. ብር 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር) ብቻ ለሎት 2. ብር 10,000 (አስር ሽህ ብር) ብቻ በሲፒኦ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን በኋላ የውል ማስከበሪያ ከመሃንዲስ ግምት 25 በመቶ በታች ካልሆነ አጠቃላይ ከተወዳደሩበት 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ በሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቹ ባቀረበው የተሰበረ ዝቅተኛ ዋጋ መስራት የሚችል መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ (conformation letter) አሸናፊነቱ በተገለጸ በ3 የሥራ ቀናት ውስጥ የማቅረብ ግዴታ ያለበት ሲሆን ይህን ማድረግ ካልቻለ ከውድድር ውጭ ሆኖ ሁለተኛ የወጣው ተጫራች የሞላው ዋጋ ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር የተሻለ ሆኖ ከተገኘ ስራው ለዚሁ ተወዳዳሪ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
  7. ከተዘጋጀው የመሃንዲስ ግምት ዋጋ አንፃር የተሰበረ ዝቅተኛ ዋጋ ከ25 በመቶ ዝቅ ብሎ በመግባት አሸናፊ ሆነው የሚመረጡ የግንባታ ተቋራጮች ውል ይዘው ወደ ስራ ሲገቡ የቅድሚያ ክፍያ እንደማይፈቀድ መታወቅ አለበት፡፡
  8.  ተጫራቹ የተሰበረ የጨረታ ዋጋ ካቀረበ ከመደበኛው 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ውጭ በእያንዳንዱ አንድ በመቶ የዋጋ ልዩነት 2 በመቶ በመጨመር በሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡
  9.  ለሎት 1. ተጫራቾች ፖስታ ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያውን በመጨመር ቴክኒካል ዶክመንቱን ለብቻ፣ ፋይናንሽያል ዶክመንቱን ለብቻ እያንዳንዱን በአንድ ፖስታ በማሸግ በማጠቃለያ ፖስታ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊው ድርጅት ውል በሚይዝበት ወቅት ውሉ ከብር 10,000,000 (አስር ሚሊዮን ብር) በላይ ከሆነ እነማይ ወረዳ ዐቃቢ ህግ የሚያስከፍለውን የአገልግሎት ክፍያ ሙሉ ወጭ መሸፈን አለበት፡፡
  10.  አሸናፊ የሆነው ተጫራች በራሱ ወጭ በእንግሊዘኛ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ እና የመሀንዲስ ግምት ከህጋዊ ትርጉም ቤቶች ወደ አማርኛ ማስተርጎም ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጅምሮ የተሞላው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ72 ቀናት ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ለሎት 1. ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ለሎት 2. ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ ፋይናንስ ቡድን ገ/ያዥ መግዛት ይችላሉ፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናውን ማስረጃ እና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸል፡፡
  12. የጨረታው መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  13. ለሎት 1. ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ21ኛው ቀን ነው፡፡ ለሎት 2. ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጎ በተመሳሳይ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኝም የጨረታውን መክፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታው ሂደት ለተላለፈው ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀን እሁድ ቅዳሜ እና የህዝብ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
  14.  አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ዋጋ ጥቅል ድምር ዝቅትኛ ዋጋ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ተጫራቾች አጠቃላይ የሥራ ዝርዝር እና ዲዛይን ከሰነዱ ጋር አብሮ የተያያዘ መሆኑን እንዲታወቅ፡፡ ለሁሉም ሎቶች በተጫራቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ እንዲሁም ፓራፍ ቢያደረግም ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡ በጨረታ ሰነዱ ዋጋ መሙያው እና ፖስታው ላይ የድርጅቱ ማህተም ስምና ፊርማ መኖር አለበት፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ
በስልክ ቁጥር 058 665 01 00 /08 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የእነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *