Be'kur (Nov 02, 2026)
ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ቤቶች ልማት ድርጅት የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ የደንብ ልብሶች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ ስፌትን ጨምሮ እንዲሁም የግንባታ ግብአቶችን፣ በቀረበዉ (ስፔስፊኬሽን) መሰረት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸዉ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአማራ ቤቶች ልማት ድርጅት ባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቀበሌ 04 ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ከሚገኘው የጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 103 በመምጣት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈልና የጨረታዉን ሰነድ በመግዛት መጫረት ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛዉ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
2. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው እና ማንኛውም የወቅቱን የመንግስት ገቢ ግብር ለመክፈሉ ወይም ሌሎች ግዴታዎችን ለመወጣቱ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
5. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
6. አሸናፊው ለአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10 በመቶ የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና (ፐርፎርማንስ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለበት፡፡
7. ከጨረታ ሳጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 106 ከረፋዱ 4፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡ 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
9. አሸናፊው ድርጅት የደንብ ልብሶችን እና ሌሎችንም በራሱ ሙሉ ወጭ በቤቶች ልማት ድርጅት ባሕር ዳር ቅ/ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
11. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 220 11 87 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአማራ ቤቶች ልማት ድርጅት ባሕር ዳር ቅ/ጽ/ቤት