Addis Zemen (Nov 03, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስታት ግንኙነት እና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ልዩ ልዩ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ፈርኒቸር እቃዎችን፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎችና የጽዳት እቃዎችን እና የተሽከርካሪ የቅባትና መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊዉ ድርጅት መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
1. በዘርፉ አግባብነት ያለዉ እና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው።
3. የግዥ መጠኑ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የሚችሉ፣
4. በግብር አመቱ ተገቢውን ታክስ እና የግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተቁ 1 እስከ 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 /አስር ቀናት ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ አራት ኪሎ በሚገኘው አልማ ህንፃ (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጀርባ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከሚገኝበት ህንጻ) ሁለተኛ ፎቅ የአብክመ የመንግስታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን የግዥ፣ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ቢሮ ቁጥር 218 በመምጣት ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይቻላል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት የቴክኒክ እና የፋይናንስ ለሚያስፈልጋቸው የቴክኒክ እና የፋይናንስ ሰነዶችን ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶችን በጥንቃቄ በፖስታ ለየብቻ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ድረስ ማስገባት አለባቸዉ። ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
8. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። ከ11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
9. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተመሰከረለት ስፒኦ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርበታል። ሲፒኦውን ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. የሚፈለጉት ዕቃዎች ዓይነት፣ ብዛትና ስፔስፍኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን።
ማሣሠቢያ፡– ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251-111-26-53 87 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የአብክመ የመንግስታት ግንኙነት እና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን
አዲስ አበባ