Be'kur (Nov 02, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 04/2019
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በ2019 በጀት አመት ለዋና ጠቅላይ መምሪያዉ አገልግሎት የሚዉሉ
- ሎት 01. የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች ፣
- ሎት 02. የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎችን ፣
- ሎት 03. የመኪና ጎማ፣ ባትሪና አላቂ የመስሪያ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዝቅተኛ ዋጋ ካቀረበዉ ድርጅት ጋር ዉል ይዞ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
4. የግዥው መጠን ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ) ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መመሪያውንና በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ ለእያንዳንድዱ ዝርዝር ሰነድ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል በአማራ ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 13 መግዛት ይችላሉ፡፡
6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ፣ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና) ማስያዝ የሚችሉ፡፡ ለጽህፈት መሰሪያዎች 60,000 (ስልሳ ሺብር)፤ ለጽዳት ዕቃዎች 50,000(አምሳ ሺ ብር)፤ ለመኪና ጎማ፣ ባትሪና አላቂ የመስሪያ ዕቃዎች 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7. በሎት 01 እና 02 ወይም የጽዳት እና የጽህፈት ዕቃዎች አሸናፊ የሚለየዉ በሎቱ ጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ላመጣ ሲሆን በሎት 03 የተገለጸዉ የመኪና ጎማ፣ ባትሪ እና የመስሪያ ዕቃ በነጠላ ዋጋ ዝቅተኛ ዋጋ ይሆናል፡፡
8. ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ በተጫራቾች መመሪያ ላይ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
9. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ማህተማቸውንና ፊርማቸውን በማስፈርና ፖስታውን በሚገባ በማሸግ በአማራ ፖሊስ ዋናው መስሪያ ቤት ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 06 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከምሽቱ 11፡00 ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በ11ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
10. የርክክብ ቦታ አማራ ክልል ዋና መስሪያ ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በግንባር በመቅረብ ይሆናል፡፡
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. በጨረታው የሚሳተፉ ድርጅቶች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ
ባህር ዳር