የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት በ3 ሎቶች የተከፈሉ ዕቃዎችን (ሎት 1: ደንብ ልብስ፣ ሎት 2: የጽህፈት መሳሪያ እና የፕሪንተር ቀለሞች፣ ሎት 3: የጽዳት ዕቃዎች) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት በ3 ሎቶች የተከፈሉ ዕቃዎችን (ሎት 1: ደንብ ልብስ፣ ሎት 2: የጽህፈት መሳሪያ እና የፕሪንተር ቀለሞች፣ ሎት 3: የጽዳት ዕቃዎች) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 03, 2026)

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አ/አ/ት/ቢ/ቦሌ/ቅ/ጽ/ቤት ግጨ/01/2019

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ ቁጥር አ/አ/ት/ቢ/ቦሌ/ቅ/ጽ/ቤት/ግጨ/01/2019

  • በሎት 1 (አንድ) ደንብ ልብስ፣
  • በሎት 2 (ሁለት) የጽህፈት መሳሪያ የፕሪንተር ቀለሞች እና
  • ሎት 3 (ሶስት) የጽዳት ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ ሲሆን፡–

የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር)፣ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፤ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ መሳተፍ ስለመቻላችሁ የሚገልጽ ማስረጃ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከስፋይነት ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባችሁ፤ ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፤

ተጫራቾች የቴክኒክና የዋጋ ፖስታቸውን ለይተው ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የቴክኒክ ፖስታው ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችና የጨረታ ማስከበሪያ መያዝ ያለበት ሆኖ በጨረታ መክፈቻ ወቅት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።

የጨረታ ሰነዱን ከአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት ከፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 602 ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 10፡00 ሰዓት በማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመግዛት መውሰድ ትችላላችሁ።

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 (አንድ) ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)፣ ለሎት 2 (ሁለት) ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) እና ሎት 3 (ሶስት) ብር 2,000.00 (ሁለት ሽህ ብር) CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

ተጫራቾች በሚሞሉት ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም እና ህጋዊ ውክልና ባለው አካል በእያንዳንዱ ገጽ ላይ መፈረም አለባቸው።

ማሳሰቢያ፡– መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡– 22 ማዞሪያ መክሊት ህንጻ ጎን ፕሪሚየም ኮሌጅ ያለበት ህንጻ ላይ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 602 ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 -10-50-28-12 መጠየቅ ይቻላል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *