Addis Zemen (Nov 02, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ
- የጽህፈት መሳሪያ፤ የፅዳት እቃዎች፤ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ቋሚ አላቂ እቃዎች፤
- የፈርኒቸር እቃ፤ ህትመት እቃዎችን፤ የመስተንግዶ፤ ደንብ ልብስ ብትን ጨረቅ እና ጫማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም፤
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ ያላቸው፣
3. የግዥ መጠኑ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች ኦሪጂናል ዕቃ መሙላት እና ያሸነፉባቸውን ዕቃ በባለሙያ ማስፈተሽ አለባቸው፡፡
6. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ የዕቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው፣
8. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይቻላል፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /C.PO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
10. ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ሲያሲዙ በፍ/ቤቱ የገቢ ደረሰኝ ቆርጦ ኮፒውን ከኦሪጂናል ሰነዱ ጋር መታሸግ አለበት፡፡
11. አሸናፊው አካል የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የሚያስዝ ይሆናል፡፡
12. ውድድሩ የሚካሄደው በጠቅላላ በሎት ድምር ነው፡፡
13. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጥቅምት/02/2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 02/2019 ዓ.ም ለ10 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
14. ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በ11ኛው ቀን ማለትም ህዳር 03/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ቀን በፍ/ቤቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
15. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0914 050 100/ 0914 050 954/ በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
16. በመ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ
አሸናፊው ድርጅት /ተጫራች ኦርጅናል ዕቃ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው እንዲሁም በፍ/ቤቱ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት