የደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2019 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ የተኝቶ ታካሚ/ህሙማን የምግብ አቅርቦት፣ የጽዳት እና የውበት አገልግሎት፣ እንዲሁም ለሰራተኞች የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ 60 ወንበርና ከዚያ በላይ የሆነ ሰርቪስ መኪና በጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ውል በመያዝ ማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2019 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ የተኝቶ ታካሚ/ህሙማን የምግብ አቅርቦት፣ የጽዳት እና የውበት አገልግሎት፣ እንዲሁም ለሰራተኞች የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ 60 ወንበርና ከዚያ በላይ የሆነ ሰርቪስ መኪና በጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ውል በመያዝ ማሰራት ይፈልጋል


Be'kur (Nov 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2019 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚዉሉ የተኝቶ ታካሚ

  • ለህሙማን የምግብ አቅርቦት፣
  • የጽዳት እና
  • የውበት አገልግሎት የሚሰጥ እና
  • ለሰራተኞች የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ 60 ወንበርና ከዚያ በላይ የሆነ ሰርቪስ መኪና በጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት ውል በመያዝ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ 

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው።
  2. የግዥ መጠኑ ብር 500‚000 (አምስት መቶ ሽህ) እና ከዚያ በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ጨረታዉ ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 (አምስት ሽ) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ሲፒኦ ኦርጅናሉን ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከፋይናስ ወይም ከዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ዉስጥ አስገበቶ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4.  ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ10 ቀን በጋዜጣ ታትሞ ቆይቶ በ11 ኛዉ ቀን ይከፈታል፡፡
  5. ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል
  6.  ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በሆስፒታሉ የስብሰባ አዳራሽ ይካሄዳል።
  7.  የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታዉን ከመክፈት አያግደዉም፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከግ/ፋ/ን/ሥ/ሂደት ቢሮ ቁጥር ማግኘት ይችላሉ :
  9. የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ከሆነ ዉድቅ ይደረጋል፡፡
  10. የጨረታ መዝጊያ ግዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታዉ እራሳቸዉን ማግለል አይችሉም፡፡
  11. የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታዉ ከተከፈተበት ቀን አንስቶ የሚቆጠር ዝቅተኛ ቀን ለ40 ቀናት ይሆናል።
  12. የጨረታ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከግ/ፋን/አ/ደ/የስ/ሂደት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 771 22 46 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  13. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
  14. አሸናፊዉ ድርጅት የውል ማስከበሪያ 10በመቶ ማስያዝ አለበት፡፡

ማሳሰቢያ፦ በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ ከጨረታ ዉጭ ያስደርጋል፤ የትኛዉም የሆስፒታሉን የጨረታ ሰነድ መገንጠል እና ማስቀረት አይቻልም፡፡

የደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *