Be'kur (Nov 02, 2026)
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሳሽ ሃና ሆቴል እቁብ ማህበር እና በአፈ/ተከሳሾች እነ ሙላት ላቀው (4ቱ) መካከል ስላለው የገንዘብ አፈ/ክስ ክርክር ጉዳይ፤ በአፈጻጸም ተከሳሾች የተወሰነባቸውን ገንዘብ በፍርዱ መሰረት መፈጸም ባለመቻላቸው ምክንያት የአፈ/ተከሳሾች ንብረት በቲሊሊ ከተማ ቀበሌ 01 የሚገኘው፤
- በአቶ ሙላት ላቀው ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በሰሜን በላቸው ደሴ፣ በደቡብ ካሳሁን በላይነህ፣ በምስራቅ መንገድ እና በምእራብ ክፍት ቦታ የሚያዋስነው 200 ካሬ ሜ. እና የካርታ ቁጥር 7980/2007 የተሰራ ቤት፣
- በአቶ መርሻ መኩሪያ ስም ተመዘግቦ የሚገኝ፣በሰሜን የትዋለ አድማስ፣ በደቡብ ጸጋየ የትዋለ፣ በምስራቅ እና በምእራብ መንገድ የሚያዋስነው፣ 500 ካሬ ሜ. የሆነ እና የካርታ ቁጥር 7424/2006 የተሰራ ቤት፣
- በአቶ እንግዳ ዘለቀ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በምስራቅ መንገድ ፣ በደቡብ አየሁ አለሙ፣ ሰሜን እና በምእራብ ክፍት ቦታ የሚያዋስነው 200 ካሬ ሜ. እና ካርታ ቁጥር 12196/12 የተሰራ ቤት፣
- በአንዷለም ፈንቴ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በሰሜን ባይህ ቤዛ፣ በደቡብ መንገድ፣ በምስራቅ አደራ በዛብህ እና በምእራብ ገበይ መልካሙ፣ የሚያዋስነው፣ 450 ካሬ ሜትር እና ካርታ ቁጥር 6160/2003 የተሰራ፤ የአራቱም ተከሳሾች ቤት መነሻ ዋጋውን ሳይጠብቅ በዜሮ መነሻ ዋጋ ሆኖ፤ የጨረታ ማስታወቂያው ከጥቅምት 23/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ
ታትሞ ቆይቶ ህዳር 23/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡30 ድረስ ይሸጣል፡፡ ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ወዲያውኑ ¼ኛውን ገንዘብ በሲፒኦ ማስያዝ የሚጠበቅባው መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ፍ/ቤት ቁጥር 2