ዳሸን ባንክ መኖሪያ ቤት ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ይሸጣል – test3.diretenders.com

ዳሸን ባንክ መኖሪያ ቤት ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ይሸጣል


Addis Zemen (Nov 02, 2026)

በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

የሐራጅ ቁጥር ዳባ/ ብማ/0042/26

ዳሸን ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የሚከተለውን የተበዳሪ አስያዥ መኖሪያ ቤት ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ይሸጣል፡፡

ተ.ቁ

የተበዳሪው ስም

አበዳሪው ቅርንጫፍ

የአስያዥ ስም

ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ

የንብረቱ

አይነት

የጨረታ

መነሻ ዋጋ

ጨረታዉ የሚካሄድበት

ከተማ

 ክ/ከተማ

የካርታ ቁጥር

የቦታ ስፋት

ቀን

ሰዓት

 ቦታ

1

አልፎዝ ኃ/የተ/ የግ/ማህበር

 

አሙዲ

ወ/ሮ አርዋ

አህመድ ኡመር

አዲስ አበባ

 

ለሚ ኩራ

ለኩራ9/29/5/37113/0487/5/01

175 ካ.ሜ

 

የመኖሪያ ቤት

 

29,825,570

24/03/2019

 

4:00-6:00

 

መኖሪያ ቤቱ በሚገኝበት አድራሻ

ማሳሰቢያ፡-

  1. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (C.P.O) በዳሽን ባንክ አማ ስም በማሰራት በጨረታው ዕለት ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
  2. ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት አድራሻ ይካሄዳል፡፡
  3. የሐራጁ አሸናፊ /ገዢ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈለው ግብር፣ ታክስ፣ ውዝፍ የሊዝ ከፍያ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) እና ሌላ ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ወጪዎችን ገዢው አሸናፊው/ ይከፍላል፡፡
  4. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑን ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ5 ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል።
  5. ባይከፍል ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያሲያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  6. በጨረታው ላይ አስያዥና ተበዳሪ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ፤ ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
  7. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሠዓት 10 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡
  8. ጨረታው ተጀምሮ በተቀመጠው ሰዓት ውስጥ ካልተጠንቀቀ ሊራዘም ይችላል፡፡
  9. ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በፅሑፍ ከባንኩ ሲደርሰው ብቻ ነው፡፡
  10. በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ አሸናፊ ባንኩ በከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡ ባንኩ ብድሩን በማናቸውም ሁኔታ ለአሸናፊው ባይፈቅድ ባይሰጥ አሸናፊው በዚህ የሀራጅ ደንብ የተቀመጡ ግዴታቸውን አያስቀርላቸውም።
  11. ባንኩ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡-

በስልክ ቁጥር፡- 0111-70-45-49 ወይም ዐ111-70-40-38 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ዳሽን ባንክ አ.ማ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *