ጢስ እሳት ውሃ ሥራዎች ኃ.የተ.የግ.ማኅበር የቁፋሮ ቢቶች እና ሲሊንደር እንዲሁም የውሃ ጉድጓድ (Borehole) ካሜራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ጢስ እሳት ውሃ ሥራዎች ኃ.የተ.የግ.ማኅበር የቁፋሮ ቢቶች እና ሲሊንደር እንዲሁም የውሃ ጉድጓድ (Borehole) ካሜራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 02, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን ጢስ እሳት ውሃ ሥራዎች የቁፋሮ ቢቶች እና ሲሊንደር እንዲሁም የውሃ ጉድጓድ (Borehole) ካሜራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ሎት

 

የእቃው አይነት

 

የጨረታ ማስከበሪያ

የማቅረቢያ ቀን

 

ሎት 1

 

የቁፋሮ ቢቶች እና ሲሊንደር

 

200,000.00

 

ከ30-45 ቀን

 

ሎት 2

 

የውሃ ጉድጓድ (Borehole) ካሜራ

100,000.00

ከ30-45 ቀን

 

ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com  ማግኘት ይችላል፡፡

የተጫራቾች መመሪያ፤

1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምሰክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የTN ሰርተፊኬት፣ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸውን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸውን ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

2. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ባሕርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ የአሸከርካሪዎች ማሠልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com  ማግኘት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዥ የተመለከተውን ገንዘብ በCPO ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለገዥ የሚከፈል (unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያወጡት ወጪ በተጫራቹ የሚሸፈን ይሆናል፡፡

6. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን እና ቴክኒካል ሰነዳቸውን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱን እቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡

7. ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ PR-03/2017 መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

8. ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 25% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊው ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡

9. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሑፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ 05 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (unconditional Bank Guarantee) በማሠራት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡

10. የማቅረቢያ ጊዜ ከላይ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው መሠረት መሆን አለበት፡፡ የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡

11. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

12. ዕቃው ወይም አገልግሎቱ የሚቀርብበት ቦታ ባሕር ዳር ከተማ የኩባንያው ጽ/ቤት መሆን አለበት፡፡

13. ማሳሰቢያ፡- እንደ ኩባንያችን ፍላጎት ውድድሩ በሎት ወይም በእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ መሠረት ሊሆን ይችላል፡፡

14. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 058-220-48-26/058-320-25-48/ በፋክስ
ቁጥራችን 058 220 48 30 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ጢስ እሳት ውሃ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማኅበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *