በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የጽዳት ዕቃዎች እና የጽህፈት መሣሪያዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የጽዳት ዕቃዎች እና የጽህፈት መሣሪያዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 04, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

  1. በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/ መንግስት የካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለደቻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የጽዳት ዕቃዎችና ጽህፈት መሣሪያ በወጣ ዝርዝር መሠረት መግዛት ስለሚፈለግ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
  2. በዚህ መሠረት በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ፡-2018/19 ዓ/ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለዉ የተ/እታ (ቫት) ምዝገባ ም/ወረቀት ያለዉ፣ የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ምወረቀት ያለዉ እንዲሁም በመንግስት ግዥ ጨረታ በአቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ የተመዘገበ ሁሉ በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ ።
  3. በተጨማሪ ጨረታዉን የሚያሸንፍ ድርጅት የጽዳት ዕቃዎችና ጽህፈት መሣሪያን እስከ ቦታዉ በማምጣትና በጥራት ኮሚቴዎችና በዘርፉ ባለሙያ ከተረጋገጠ በኋላ ክፍያ የሚፈጸም መሆኑን የሚያምን
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 15 ኛዉ ቀን ድረስ ለወረዳዉ ገቢዎች ጽ/ቤት የማይመለስ 500 ብር በፊደል አምስት መቶ ብር ብቻ በመክፈል ከመ ቤታችን ግዥ ኬዝ ቲም ሰነድ በመዉሰድና በዝርዝሩ መሰረት ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመዉሰድ ከተእታ ቫት/ ጋር በመሙላት እንዲሁም ከላይ የተዘረዘሩ የንግድ ፈቃድና ተያያዥ የመረጃ ኮፒዎችንና የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ በአንድ ፖስታ በማሸግ  ዋጋ የተሞላበትን ኦሪጂናል ኮፒዉን የጨረታ ሰነድ በሌላ ፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠሩ ተከታታይ ቀናት እስከ 15ኛዉ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታዉ በዕለቱ 8፡30 ላይ ይከፈታል ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል፡፡
  6.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሽህ ብር ብቻ/ በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፦
  7. በጨረታ አከፋፈት ወቅት የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታዉን አከፋፈት ሂደት አያስተጓጉለዉም፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ ::
  9. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0945927114 ደዉለዉ መረዳት ይችላሉ፡፡

በደ/ም/ሕ/ክ/መ/ካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት (አውራዳ)


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *