Addis Zemen (Nov 04, 2026)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሰሜን ወሎ ዞን ገ/ኢ/ል መምሪያ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር ቡድን ለሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል
- ሸድ ግንባታ ከደረጃ 5 እና በላይ ያሉትን GC ስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች መምሪያው ባወጣው የሸድ ግንባታ ፍላጎት ዝርዝር መግለጫ መሰረት የመጫረቻ ሰነዳችሁን በቴክኒካልና ፋይናንሽያል በሚል ተለይቶ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በጥንቃቄ ሞልቶና በፖስታ አሽጎ በማቅረብ መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን በጨረታው ለመሳተፍ ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች
በዚህም መሰረት ተጫራቾች ማሟላትያለባቸው ፡–
- በዘርፉ የተሰማሩና ህጋዊ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ሰርተፊኬት/ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /tin number/ ፤የግብር ከሊራንስ ማቅረብ የሚችልና QR ደረሰኝ ያለው
- ተጫራቾች ከደረጃ 5 እና በላይ የሆኑና የጠቅላላ ስራ ተቋራጭ /GC/ ፍቃድ ያላቸውና የመልካም ስራ አፈጻጸም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 2 የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከቴክኒካል መጫረቻ ሰነዶቻችሁ ጋር አያይዛችሁ ማቅረብ ይኖርባችኋል
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00/ሃምሳ ሺህ ብር /በCPO፤ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣ሌተር ኦፍ ክሬዲት/letter of credit/ እና ከጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተሰጠ የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና ደብዳቤ ከጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋር የተወሰደው የገንዘብ መጠንን በማስጠቀስ በፖስታ ውስጥ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ማንኛውም ግብርና ታክስ አካቶ መሙላት አለባቸው
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርበው 10% ዋስትና በማስያዝ ውል መፈጸም አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ73 ቀን የሚቆይ ሆኖ መሰራት አለበት
- የጨረታ ሰነዱ ከ 25/ 02/2019 ዓ.ም እስከ 14/ 03/2019 ዓ.ም ድረስ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ የታደሰ ንግድ ፍቃዱን በመያዝ ባለቤቱ /ህጋዊ ውክልና ያለው በአካል ሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ፋይናንስ ቡድን በመቅረብ መግዛት የሚችሉ መሆኑን አውቀው በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ዋጋ ሞልተው ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ14/03/2019 ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የማይገኝ ተጫራች በተገኙት ስምምነት ይከፈታል፡፡ ባይገኝም በህግ ተገዥይሆናል
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ የቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ፤ የፋይናንሽያል ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በሚል ተለይቶ ሁለቱም አይነት ፖስታ ላይ ንግድ ፍቃድና ቲን ነምበር፤ ቫት አብሮ ተያይዞ መቅረብ አለበት
- ተጫራቾች በሁሉም የጨረታ ሰነዳቸው ላይ ክብ ማህተምና ፊርማ መፈረም ይኖርባቸዋል
- ውድድሩ በሎት ወይም በድምር ዋጋ ስለሆነ ሁሉም የግንባታ ስራ ዝርዝር ዋጋ መሞላት አለበት
- አሸናፊው አካል በፍትህ ውለታ በመውሰድ /በመያዝ/ ግደታው መሆኑን ግንዛቤ መያዝ ይኖርበታል
- ከጨረታ ሰነዱ ጋር የተያያዘውን የተጫራቾች መመሪያ በደንብ በማንበብና በመረዳት ዋጋ መሙላት ይኖርባችኋል
ማሳሰቢያ፡–
- የተጫራቾች ዋጋ መሙሊያ ሰነድ ላይ የአንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ
- ቲን ነምበር፣ ንግድ ፈቃድ እና የቫት የምስክር ወረቀት ለየብቻ በአንድ አንድ ገጽ ኮፒ ተደርጎ መያያዝ አለበት
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ መክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል
- በውክልና ጨረታ ሰነድ የሚገዛ አካል ኦሪጅናል የፍትህ ውክልና ይዞ መቅረብ ይኖርበታል ውክልናውም አቻና ከዚያ በላይ መሆን አለበት
- በቴክኒካል መስፈርቱ 70% እና ከዚያ በላይ ነጥብ ያመጣ አካል ብቻ ወደ ፋይናንሻል ውድድር የሚገባ መሆኑ ይታወቅ
ለበለጠ መረጃ በስል ክቁጥር ፡– (0333311597/2680) ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሰሜን ወሎ ዞን ገ/ኢ/ል መምሪያ የግዥ / ፋይ / ንብ/አስ/ር ቡድን