Addis Zemen (Nov 04, 2026)
በድጋሚ የወጣ የብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሠራተኞች ኃላፊነቱ የተወሰነ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበር በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር NCB-002-2019 የኮፊ ሀውስ እቃዎች (ሎት 1)፣ የኤሌክትሪክ ማሽኖች ዕቃዎች (ሎት 2) እና የፅዳት አገልግሎት ዕቃዎች (ሎት 3) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡–
1. በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid Trade Licensee)
2. የታክስ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት
3. የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ (VAT Certificate)
4. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ፈቃድ (Valid Tax Clearance Certificate):
5. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10% በማቅረብ በግልፅ ጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ። በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጠዋት 3፡00 – 6፡00 ከሰዓት 7፡00-10፡00 ሰዓት ብቻ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስትት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በሸጎሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ ብሮድካሰቲንግ ኮርፖሬሽን ሠራተኞች ኃላፊነቱ የተወሰነ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበር ሱቅ መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት እስከ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፤ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡ 0913 222 338, 0911 045 952, 0913 236 539
አድራሻ:- ከአዲሱ ገበያ ወደ ዊንጌት በሚወስደው መንገድ ላይ ሸጎሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ ብሮድካሰቲንግ ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሠራተኞች ኃላፊነቱ የተወሰነ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበር