ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የፓወር ፋክተር ኮሬክተር (Power Factor Corrector) ጥናት፣ አናሊሲስ፣ ዕቃ አቅርቦት እና ገጠመኝ ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የፓወር ፋክተር ኮሬክተር (Power Factor Corrector) ጥናት፣ አናሊሲስ፣ ዕቃ አቅርቦት እና ገጠመኝ ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 04, 2026)

የፓወር ፋክተር ኮሬክተር ግዢ

የወጣ ግልፅ ጨረታ

ድርጅታችን ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የፓወር ፋክተር ሬክተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገጠም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች የፓወር አክተር ኮሬክተር ለመግጠም የጥናት አናሊሲስ በመስራት የእቃው ዋጋ እና የሙያው ዋጋ ከነ ሙሉ ዕቃው በማቅረብ ሥራውን ሰርቶ ለማስረከብ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል አስሮ ማስራት ስለሚፈልግ፤

በዚሁ መሰረት

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል 2ኛ ፎቅ ከፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 7 መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 /ሰባት/ ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሠነድ በመግዛት አናሊሲስ ለመስራት በድርጅቱ ሰው ሃይል አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ የማሽኖቹን ጥናት ፋሲሊቲ ሰርቪስ በተገኙበት መውሰድ ይችላሉ::
  3. ተጫራች የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርፍተኬት ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል፡
  4. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20 (ሀያ ሺ) በይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ሥም ሲፒኦ (CPO) በማሰራት ማስያዝ ይኖርበታል።
  5. ተጫራች ከዚህ በፊት በዚሁ ሥራ በጨረታ የተሳተፈባቸው ድርጅቶች (መ/ቤቶች) የመልካም የሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  6. ተጫራች የሚያቀርበውን የጨረታ ሰነዱ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ለየብቻ ለይቶ በማሸግና በኢንቨሎፑ ላይ የተጫራች ማንነት በመግለፅ ክብ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  7. ተጫራች ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ካላሟላ ከጨረታው የሚሰረዝ ይሆናል፡፡
  8. በጨረታ ማስታወቂያ እና ዶክመንቱ ላይ የተገለፁትን የመወዳደሪያ ነጥቦቹን ያሟሉ ተጫራቾች ብቻ ወደ ፋይናንሻል ግምገማ ያልፋሉ፡፡
  9. ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 7 /በሰባተኛው የሥራ ቀን በስራ ሰዓት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 7 /በሰባተኛው የሥራ ቀን/ በስራ ሰዓት ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ይሆናል፡፡
  11. ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ መገኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡– አዲስ አበባ ስቴድየም ቤተ ዛታ ሆስፒታል ፊት ለፊት “ይሓ ሲቲ ሴንተር ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር – 12

ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር– የቢሮ 0115580129/0115576954/

ሞባይል – 0922079575 /0911397239

ማሳሰቢያ፡– ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *