Addis Zemen (Nov 05, 2026)
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በወረጃርሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ለወረጃርሶ ወረዳ ከተማ አስተዳደር የመንገድ ስራ መብራት /paawuzaa/ Street light Smart Pole Construction/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች
1. በዘርፋ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር ግዴታውን የተወጣ ስለመሆኑ የሚገልጽ በቂ የግንባታ መረጃ ሊኖረው ይገባል።
2. የብቃት መረጋገጫ ስራ እና የደረጃ ብቃት አነስተኛው መነሻው Electro Mechanical Work Grade Two /EMW—2/ እና ከዚያ በላይ ያለው።
3 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 21 የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሆኖ የማይመለስ 5,000 (አምስት ሺህ/ የኢትዮጵያ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ወረጃርሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 12 በአካል በመገኘት መግዛት ይችላሉ።
4. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ22ኛው የስራ ቀን ከሰዓት በ8፡00 ሰዓት ድረስ ኦሪጂናል እና ኮፒውን በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ በወረጃርሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዚሁ ስራ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ22ኛው ቀን የስራ ሰዓት በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች በሰዓቱ ባይገኙም ጨረታው በተባለው ሰዓት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው በሌሉበት ይከፈታል።
7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. 22ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
ተጫራቾች ግልጽ ያልሆነላቸው ሃሳብ ካለ በስልክ ቁጥር፡- 0985376746 ፣ 0947546647፣ 0969148899 – በመደወል መጠየቅ ይቻላል በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በወረጃርሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት እቃ ግዢ ክፍል በአካል ቀርበው መረዳት ይችላሉ።
በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በወረጃርሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት