የብርብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት ዩኒት በ2019 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች የሚውል የጽህፈት መሣሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የብርብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት ዩኒት በ2019 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች የሚውል የጽህፈት መሣሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 05, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የብርብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት ዩኒት በ2019 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች

1. የጽህፈት መሣሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመገዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ተጫራቾች:-

1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ፤

2. የግብር ክፈይነት ቲን ነምበር ያለው፤

3. በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ፤

4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፤

5. የመኪና ኪራይ የጫኝ እና አውራጅ በአሸናፊ ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል።

6. ንብረቶችን አስከ ብርብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት ዩኒት ግቢ ደረስ ለማድረስ ፍቃደኛ የሆነ

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለጽህፈት መሣሪያና ለአላቂ የቢሮ ዕቃ ግዥ ብር 10 አስር ሺህ ብር ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

8. ተጫራቾቾ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በብርብር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ዩኒት በመቅረብ የማይመለስ 300 (ሦስት መቶ ብር ብቻ ለጨረታ ሰነድ በመክፈል እና ደረሰኝ በመያዝ የጨረታ ዝርዝር የያዘውን ሰነድ ከብርብር ከተማ አሰተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት ዩኒት 1ኛ ፎቅ ከቢሮ ቁጥር 01 መግዛት ይቻላል።

9.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናሉንና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ ሙሉ አድራሻውን በመግለጽ በአንድ እናት ፖሰታ በመክተት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን አንዲጨምሩ እያሳሰብን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይታሸጋል። የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተጠቀሰው በሥራ ሰዓት ይታሸጋል።

10.ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ልክ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።

11. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት የአሸናፊነት ደብዳቤ በተጠቀሰው በ7ኛው ቀን የውል ማስከበሪያ 10% በመያዝ ውል ይፈራረማል።

12. የጨረታ ሣጥን በብርብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት ዩኒት 1ኛ ፎቅ በቢሮ ቁጥር 01 ላይ ይገኛል።

13. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።

የብርብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት ዩኒት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *