Addis Zemen (Nov 05, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እነ ሂሩት አበበ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ብሩክ ጌታቸው መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/105552 በ25/10/2018 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/107523 በ27/11/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 የቤት ቁ/692 የካርታ ቁጥር 4/31/53/00 እና በእነ አቶ ጌታቸው አበበ ወልዴ የተመዘገበ ቤት እና ይዞታ የቦታ ስፋት 89 ካ/ሜ የውስጥ ለውጥ መንገድ 17 ካ/ሜ ይነካዋል፤ ይዞታው ጉቶሜዳ (LOCAL DEVELOPMENT PLAN) ጥናት ውስጥ የሚገኝ ካርታ ያለው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 2,889,346 ( ሁለት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰማንያ ዜጠኝ ሺህ ሶስት መቶ አርባ ስድስት) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤጽ/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት