Addis Zemen (Nov 05, 2026)
የማሽነሪ እና ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ
በድጋሚ የወጣ ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 07/2019 ዓ.ም
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ለመንድ ጥና እና ለሚገነቡ መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
- ተጫራቾች የሚጠበቅባቸውን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፣
- የግዥው መጠን ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- ለኪራይ የሚቀርቡት ማሽነሪ እና ተሽከርካሪዎች የፈረስ ጉልበታቸው፣ የስሪት ዘመናቸውና ሌሎች ከጨረታ ሰነዱ የተገለፁት መስፈርቶች ተሟልተው ማቅረብ አለባቸው፣
- ለኪራይ የሚቀረቡት ማሽነሪ እና ተሸከርካሪ ኪሎ ሜትር(ስዓት) እና የነዳጅ ቆጣሪው በትክክል የሚሰራ መሆን አለበት፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለማሽነሪዎች የጠቅላላ ዋጋዉን 1% ሆኖ ለሌሎች ተሽከርካሪዎች ለእያንዳንዱ ብር 10,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ከፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብሔራዊ ባንክ እውቅና ከሰጣቸው ባንኮች ብቻ ማስያዝ አለባቸዉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ስም በተከፈተው በኢትዮጵያ ንገድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኮፒውን በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ26/02/ 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 06/03/2019 ዓ.ም ዋናው መ/ቤት ባህርዳር በአካል በመገኘት መግዛት ይችላሉ፣
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻሉንና ቴክኒካሉን በአግባቡ በፖስታ በማሸግ የተሟላ አድራሻ በመፃፍ በሁለት ፓስታ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ ተዘጋጅቶ ከግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 06/03 2019 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ በአካል በመገኘት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ኤጄንሲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ወይም ከግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 03 በ06/03/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል። እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- የዋጋ መሙያ ቅፁ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታው ውድድር ውጭ ይደረጋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058-320-5555 ወይም 058-222-1107 በመደወል ወይም በኤጀንሲው ደህረ ገጽ www.arrca.gov.et ማግኘት ይችላሉ።
የአብክመ ገጠር መንገድች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
ባህር ዳር