Addis Zemen (Nov 05, 2026)
ግልጽ የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
የአብክመ ግብርና ቢሮ በክልሉ በሚገኙ ወረዳዎች ሊያሰራ በያዛቸው የቨርሚ ኮመፖሰት ሼድ ግንባታ እና ተያያዥ ስራዎችን ፣ በግንባታ ዘርፉ የተሰማሩ ተቋራጮችን በሚከተሉት መስፈርቶች በመለየት በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
- ደረጃቸው GC‐4/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆነ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር / Tin Number ያለውና ማቅረብ የሚችል፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣ በስራና ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተመዘገቡና የታደሰ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤ በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የተመዘገበና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው መረጃ የሚያቀርቡና እና በጨረታ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልፅከገቢዎች የተሰጠ የምስክር ወረቀት የሚያቀርብ፣
- በክልሉና በቢሯችን ውስጥ በግንባታ ስራ ተሰማርተው ከሆነ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ያላቸውና ስራዎችን ያላስተጓጎሉ ወይም ያላቋረጡ፤
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጡትን የቴክኒክና የገንዘብ መመዘኛዎችን የሚያሟሉ ስራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ስራ ሂደት ዘወትር በስራ ስዓት በመቅረብ ለአንድ ሳይት የማይመለስ 1000 (አንድ ሺ) ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በመውሰድ ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አነድ ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ የጨረታ ሰነድ እንዲሁም የጨረታ ዋስትናም ለብቻው እያንዳንቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ አንድ ላይ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት እስከ 20ኛው ቀን ይሆናል።
- ኦርጅናል ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ በሚታይ መልኩ በድጋሚ መፃፍ አለበት ፣ በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ የተቋራጩ ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት። ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለ ከ20 ተከታታይ ቀን በኋላ በ21ኛው ከን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 200,000 (ሁለት መቶ ሺ) ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የክፍያ ማዘዣ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የባንክ ዋስትና ሲሆን ይህም 45+28(73)ቀን የሚቆይ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ከቀረቡት ሣይቶች ውስጥ የሚጫረቱበትን ላይት ለይተው በግልፅ በመፃፍ መለየት አለባቸው።
- አንድ ተጫራች ከአንድ እስከ ሶስት ባሉ ሳይቶች ላይ መወዳደር የሚቻል ሲሆን ከአንድ ሳይት በላይ ለሚጫረት ተቋራጭ ለእያንዳንዱ ሣይት የተሟላ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅበታል። ቢሮው የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ከቢሮው ጋር ሌላ ፕሮጅክት ያላቸው ከሆነ እየተሰራ ያለው ግንባታ 80% እና ከዚያ በላይ የደረሰ መሆን አለበት።
- የመወዳደሪያ ሳይቶቹም የሚከተሉት ናቸው።
|
ሎት |
የፕሮጀክቱ መገኛ ቦታ |
የጨረታ ማስከበሪያ (ብር ) |
|
1 |
ምስ/ጎጃም ዞን፣ ሸበል ወረዳ፣ ትኬ ቀበሌ፣ ጭሟገል ች/ ጣቢያ |
200,000.00 |
|
2 |
ምስ/ጎጃም ዞን፣ ደጀን ወረዳ፣ ሞዠን ቀበሌ፣ ጢቅ ች/ጣቢያ |
200,000.00 |
|
3 |
ምዕ/ጎጃም ዞን፣ወንበርማ ወረዳ፣ ሽንዲ ቀበሌ ወይኒቱ ች/ጣቢያ |
200,000.00 |
|
4 |
ምዕ/ጎጃም፣ደንበጫ ወረዳ፣ ለጀት ቀበሌ ጉላ ች/ ጣቢያ |
200,000.00 |
|
5 |
ሰ/ጎጃም ዞን፣ደቡብ አቸፈር ወረዳ፣ ቀልጣፋ ቀበሌ፣ ክልቲ ች/ጣቢያ |
200,000.00 |
|
6 |
አዊ ብ/ዞን፣ ዳንግላ ወረዳ፣ ጊሣ ቀበሌ ሣሣራ ች/ጣቢያ |
200,000.00 |
|
7 |
አዊ ብ/ዞን፣ ጓጉሳ ወረዳ፣ ጅባይታ ቀበሌ ጅባይታ ች/ጣቢያ |
200,000.00 |
|
8 |
ደ/ጐንደር ዞን፣አንዳቤት ወረዳ፣ ወለሽ ከተማ FTC |
200,000.00 |
|
9 |
ደ/ጐንደር ዞን፣ ፎገራ ወረዳ፣ ቆሃር ቀበሌ ቆሃር ች/ጣቢያ |
200,000.00 |
|
10 |
ማዕ/ጎንደር ዞን፣ምዕ/ደንቢያ ወረዳ፣ ተዘባ ቀበሌ መልካም ውኃ |
200,000.00 |
|
11 |
ማዕ/ጎንደር ዞን፤ነባሩ ጭልጋወረዳ፣ ጫንድባ ቀበሌ ጫንድባ ች/ጣቢያ |
200,000.00 |
|
12 |
ሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ፣ አዲስጌ ቀበሌ አዲስጌ ች/ጣ |
200,000.00 |
|
13 |
ሰ/ሸዋ ዞን፤ኤፍራታና ግድም ወረዳ፣ ላይኛዉ አጣዬ ቀበሌ፣ ፈረደ ውኃች/ጣ |
200,000.00 |
|
14 |
ሰ/ሸዋ ዞን፤መንዝ ማማ ወረዳ፣ ቀበሌ ዐ2፣ አምቦ ዉኃ ች/ጣ |
200,000.00 |
|
15 |
ደ/ወሎ ዞን፣ ቃሉ ወረዳ፣ 032 ቀበሌ፣ FTC |
200,000.00 |
|
16 |
ደ/ወሎ ዞን፣ ጃማ ወረዳ 06 ቀበሌ፣ FTC |
200,000.00 |
|
17 |
ሰ/ወሎ ዞን፣ መቄት ወረዳ 07/በረከዝ ቀበሌ፡ በረከዝ ች/ጣቢያ |
200,000.00 |
|
18 |
ሰ/ወሎ ዞን፣ ሀብሩ ወረዳ/ ገራዶ/ዐ4 ቀበሌ ገራዶ ች/ጣቢያ |
200,000.00 |
|
19 |
ኦሮሞ ብ/ዞን፣ ዳዋጨፋ ወረዳ፣ ሲትር ቀበሌ፣ ሲትር ች/ጣቢያ |
200,000.00 |
|
20 |
ዋግ/ብ/ዞን፣ ሰቆጣ ከተማ: ዐ16/ፈቅረ ሰላም/ ቀበሌ፣ ሩባሪያች/ጣቢያ |
200,000.00 |
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251-0582-26-2891 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ. በአብክመ ግብርና ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት፤ ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በአብክመ ግብርና ቢሮ ግዥና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት