Addis Zemen (Nov 06, 2026)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/GBP/NCB/05/2019
1. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለጊቤ 3 እና ጊቤ 2 ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች
- በሎት–1 የመኝታ ቤት፣የሳሎን እና የምግብ ቤት ዕቃዎች፤
- በሎት-2 ፍራሾች እና የመስኮት መጋረጃዎች ፣
- በሎት-3 የማብሰያ ቤት እና የልብስ ማጠቢያ ዕቃዎች ፣
- በሎት-4 የውሃ ማሞቂያ እና የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ዕቃዎች እና
- በሎት-5 የመካከለኛ ክሊኒክ ዕቃዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
2. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደለ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት የአቅራቢዎች የአገልግሎት ስጪዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ መሆን አለባቸው።
3. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሰው ኃይልና ፋይናንስ አስተዳደር ህንጻ 2ኛ ፎቅ ካሼር ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ህዳሴ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ከጀነሬሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ ቁጥር 114 መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን የቤት ዕቃዎች በሚመለከት የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ፖስታ የጨረታ ቁጥር EEP/GBP/NCB/05/2019 የሚል ምልክት በማድረግ 1(አንድ) ኦሪጂናል እና 2 (ሁለት) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ከዚህ በታች በተገለጸው ሰንጠረዥ መሰረት ለ90 / ዘጠና/ ቀን የአገልግሎት ጊዜ የሚቆይ የባንክ ክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power) ስም የተዘጋጀ ማቅረብ አለባቸው።
|
የሎት ቁጥር |
የግዥው ዓይነት |
ጨረታው ማስከበሪያ መጠን /በብር/ |
ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት |
ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት |
|
ሎት-1 |
የመኝታ ቤት፣የሳሎን እና የምግብ ቤት ዕቃዎች ግዥ |
ብር 800,000.00 |
ህዳር 28 ቀን 2019 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት |
ህዳር 28 ቀን 2019 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት |
|
ሎት-2 |
ፍራሾች እና የመስኮት መጋረጃዎች ግዥ |
ብር 400,000,00 |
||
|
ሎት 3 |
የማብሰያ ቤት እና የልብስ ማጠቢያ ዕቃዎች ግዥ |
ብር 600,000.00 |
||
|
ሎት 4 |
የውሃ ማሞቂያ እና የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ዕቃዎች ግዥ |
ብር 100,000.00 |
||
|
ሎት 5 |
የመካከለኛ ክሊኒክ ዕቃዎች ግዥ |
ብር 100,000.00 |
6. ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
7. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011 557 4011 መደወል ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል