የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ያገነባቸውን ዘመናዊ ህንፃዎች ውስጥ ለመኖሪያ/ገስት ሃውስ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶችን በውጪ ምንዛሬ ተመን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ያገነባቸውን ዘመናዊ ህንፃዎች ውስጥ ለመኖሪያ/ገስት ሃውስ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶችን በውጪ ምንዛሬ ተመን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 06, 2026)

የ9ኛ ዙር የመኖሪያ/ገስት ሀውስ ቤቶች የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ፌቤ.ኮ/ ብ.ግ ጨ/አገ/17/02/2019

1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ካስገነባቸው ዘመናዊ ህንፃዎች ውስጥ ለመኖሪያ ገስት ሃውስ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶችን በውጪ ምንዛሬ ተመን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ. ጨ/አገ/17/02/2019 ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

2. ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የመኖሪያ ገስት ሃውስ ቤቶች ክራይ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የመወዳደሪያ ተመን ዋጋ በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡

3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ ሥርዓትና ይኸንኑ አስመልክቶ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መመሪያ መሰረት ነው፡፡

4. ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች የተሟላ የጨረታ ሰነዱን ከጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ 2፡00 እስከ 11፡00 ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ድረስ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በካሽ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድን በኮርፖሬሽኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በሚገኘው ዋና የመሰብሰቢያ አዳራሽ 1ኛ ፎቅ ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ወይም ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሀምሳ ሺህ ብር/ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ሲ.ፒ.ኦ በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፣ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ክፍል 1 ላይ በተገለፀበት ቀንና ሰዓት ይከፈታል።

6. ተጫራቾች ቤቶቹን በአካል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ማብቂያው ቀን ድረስ በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ቤቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ድረስ በመቅረብና ለዚሁ ስራ በሚመደቡ ባለሙያዎች እና በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ቤቶቹን መመልከት ይችላሉ።

7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ

በስልክ ቁጥር 0910-48-59-48 ወይም 0922-98-76-33 ወይም 0922-49-18 85 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ዌብሳይት/ website www.fhc.gov.et

P.O. Box 299

ፋክስ ቁጥር፡ 011-5-54-60-45/ 0115-52-46 46

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *