በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቱሪዝም ቢሮ የገልማ አባ ገዳ ማዕከል በስሩ ለሚያስተዳድረው ካፍቴሪያ አገልግሎት የተለያዩ ግብአቶችን መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቱሪዝም ቢሮ የገልማ አባ ገዳ ማዕከል በስሩ ለሚያስተዳድረው ካፍቴሪያ አገልግሎት የተለያዩ ግብአቶችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 07, 2026)

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቱሪዝም ቢሮ የገልማ አባ ገዳ ማዕከል በስሩ ለሚያስተዳድረው ካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውሉ ከታች በተዘረዘረው መሰረት በንግድ ዘርፉ የተሰማሩ ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈጸም ስለሚፈልግ ተፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶችን /ግለሰቦችን/ ለ1 (አንድ) ዓመት ውል በመግባት ግዥ መፈጸም ስለሚፈልግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል /ጥሪ ያደርጋል ፡፡

የዕቃዎቹ ዝርዝር

  • ሎት 1፤-የምግብ ግብዓቶች ፤ አትክልትና ፍራፍሬ
  • ሎት 2፡- ወተትና የወተት ተዋጽኦ ወዘተ
  • ሎት 3፡- ሌሎች የምግብ እህሎች /የእንጀራ ሩዝ፣ገብስ ፤የዳቦ ስንዴ ዱቄት፣ እና ሌሎች የፋብሪካ ምርቶች
  • ሎት 4 የዶሮ ስጋ፤የዓሳ ስጋ፤ እንቁላል፤

በዚሁ መሰረት፦

1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15) ተከታታይ ቀናት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቱሪዝም ቢሮ የገልማ አባ ገዳ ማዕከል ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 110 የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር / በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ 

3, የጨረታ ሠነዱ ይህ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ አምስተኛው (15)ኛው ተከታታይ ቀናት ይሸጥና በአስራ ስድስተኛው (16)ኛው የስራ ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡

4. አሸናፊው ድርጅት ለውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ላይ አስር ከመቶ(10/100 ) በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለበት።

5. የውል ማስከበሪያውም አሸናፊው ድርጅት ዕቃዎቹን በውሉ የጊዜ ገደብ አስገብቶ እስኪያጠናቅቅ ድረስ ተይዞ የሚቆይ ይሆናል፡፡

6. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች ለማቅረብ ለı (አንድ) ዓመት ውል መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡

7. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች በራሳቸው የትራንስፖርት ወጪ ጭነው አዳማ ገልማ አባ ገዳ ማዕከል ጽ/ ቤት ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

8.ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን በተናጠል በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ የድርጅቱ ማህተም አርፎበት መ/ቤቱ ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በጨረታው የመክፈቻ እለት ማስገባት አለባቸው፡፡

9. ሌሎች ዝርዝር ማብራሪያዎች ከሚሸጠዉ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቸላሉ፡፡

10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡  ስልክ ቁጥር፡- 022 112 45 65/022 212 92 55 ደውለው አስፈላጊን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቱሪዝም
ኮሚሽን የገልማ አባገዳ ማዕከል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *