ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ. ለሚሰጠው የብድርና ቁጠባ አገልግሎት የሚጠቀምባቸውን የተለያዩ ጥራዞች፤ ቅጾች፤ ፎርሞችና ሾውቸሮች የህትመት አገልግሎት ፍላጎት ካላቸው የሀገር ውስጥ ማተሚያ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ. ለሚሰጠው የብድርና ቁጠባ አገልግሎት የሚጠቀምባቸውን የተለያዩ ጥራዞች፤ ቅጾች፤ ፎርሞችና ሾውቸሮች የህትመት አገልግሎት ፍላጎት ካላቸው የሀገር ውስጥ ማተሚያ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 07, 2026)

የህትመት አገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ

ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ. ለሚሰጠው የብድርና ቁጠባ አገልግሎት የሚጠቀምባቸውን የተለያዩ ጥራዞች ፤ ቅጾች ፤ ፎርሞችና ሾውቸሮች የህትመት አገልግሎት ፍላጎት ካላቸው የሀገር ውስጥ ማተሚያ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል፡፡ የስራው ዝርዝር እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

ተቁ

 

የሚታተሙት ሰነዶች ዝርዝር

 

መለኪያ

 

ብዛት

 

መግለጫ

 

1

የተለያዩ ጥራዞች ህትመት

 

ጥራዝ

 

7000

የተለያየ መጠን ያላቸው

 

2

የተለያዩ ቅጾች/ ፎርሞች ህትመት

 

ቁጥር

 

135000

የተለያየ መጠን ያላቸው

 

3

የተለያዩ የቁጠባ እና የብድር ደብተሮች

 

ቁጥር

 

50000

መጠናቸው ይለያያል

 

4

ሰርተፊኬት

 

በቁጥር

 

5000

 

በመሆኑም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች የሚከተሉትን ህጋዊ ሰነዶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡

  • የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ ቫት ምዝገባ ማረጋገጫ ፤ የታክስ ክሊራንስ፤ የታክስ ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የቫት ደረሰኝ እና ሌሎች አስፈለጊ መረጃዎች ፤ የስራ ልምድን ጨምሮ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  • ጨረታው ጸንቶ የሚቆየው ለ10 (አስር) የስራ ቀናት ነው፡፡ ማለትም ከጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ሆኖ የጨረታ ማስረከቢያ ቀን ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ነው።
  • ሰነድ ለመግዛት የምትፈልጉ ሰነዱ በሚገኝበት በቡሳ ጎኖፋ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ዋናው መስሪያ ቤት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ( ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት በተጫረቱበት ዋጋ ብር 10 ፐርሰንት ( አስር በመቶ) በሲ.ፒ.ኦ
    በማቅረብ ይሆናል፡፡
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ (ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ) ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስገቢያ ጊዜ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡሳ ጎኖፋ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ
  • ዋናው መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይሆናል። ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • በጨረታው ያሸነፈ/ፉ ተጫራች/ቾች የጨረታው ውጤት በታወቀ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ውል መፈረም አለባቸው፡፡ አድራሻ፦ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት ፤ ቤተ ሳ ይ ዳ ህንጻ 4ኛ ፎቅ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ (አ.አ)::

ስልክ ቁጥር፡-0114 16 25 36/ 0936 784 833
ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *