የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በካፒታል ፕሮጀክት ተገንብተው በተለያዩ ሳይቶች የሚገኙ በጋራ ህንጻዎች ስር የሚገኙ ንግድ ቤቶችን በ3ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በካፒታል ፕሮጀክት ተገንብተው በተለያዩ ሳይቶች የሚገኙ በጋራ ህንጻዎች ስር የሚገኙ ንግድ ቤቶችን በ3ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 07, 2026)

ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በአዋጅ ቁጥር 84/2016 በአንቀጽ 55 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በጋራ ህንጻዎች ስር የሚገኙ ንግድ ቤቶችን በጨረታ እንደሚሸጥ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት በካፒታል ፕሮጀክት ተገንብተው በተለያዩ ሳይቶች የሚገኙ ንግድ ቤቶችን በ3ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ኮርፖሬሽኑ በግልጽ ጨረታ ያቀረባቸውን ንግድ ቤቶች ተወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከ25/02/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 18/03/2019 ዓ.ም ድረስ ባሉት 21 የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ) ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ምሽት 11፡30 ድረስ በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ/ በመክፈል ከዚህ በታች በተገለፁት ቦታዎች የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ተ.ቁ

የጨረታ ሰነድ መሸጫ ሥፍራዎች

የሚገኝበት አድራሻ

1

አዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት

ባምቢስ ግሪክ ትምህርት ቤት አካባቢ

2

ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሰሜን ቅርንጫፍ

ለሚኩራ ክ/ከተማ ቦሌ አራብሳ ሰፈራ አደባባይ አካባቢ

3

ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ደቡብ ቅርንጫፍ

ንፋስ ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ፉሪ ሃና ሳይት

4

ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ

ለሚ ኩራ ክ/ከ ቦሌ አያት 49 ሳይት

5

ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምዕራብ ቅርንጫፍ

አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወርቁ ሰፈር

በተጨማሪም በኮርፖሬሽኑ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *