የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ የ2019 በጀት ዓመት የቢሮ አላቂ እና ቋሚ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ የ2019 በጀት ዓመት የቢሮ አላቂ እና ቋሚ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 07, 2026)

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር LHR/A/NCD/001/2019 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ የ2019 በጀት ዓመት የቢሮ አላቂ እና ቋሚ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሚገዛው ዕቃ ተዛማጅ አገልግሎት

  • ሎት 01፡- ኮምፒውተር፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ
  • ሎት 02፡- የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ
  • ሎት 03፡- የመኪና ኪራይ
  • ሎት 04፡- የቢሮ ማስዋቢያ እቃዎች ምንጣፍ እና መጋረጃን ጨምሮ
  • ሎት 05፡- የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ
  • ሎት 06፡- የደንብ ልብስ ግዥ
  • ሎት 07፡- ሌሎች የቢሮ መገልገያ እና የጄኔሬተር መለዋወጫ እቃዎች ግዥ
  • ሎት 08 ፡-የህትመት ግዥ
  • ሎት 09፡- የመኪና ጎማና ጌጣጌጥ እቃዎች
  • ሎት 10፡-የቅየሳ መሳሪያ ኪራይ

በመሆኑም በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች፡-

1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ እና በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1፡ 30,000 ብር/ ሰላሳ ሺህ ብር/ ለሎት 2፡- 10,000 ሺህ ብር /አስር ሺህ ብር/ ለሎት 3፡- 80,000 ሺህ ብር /ሰማንያ ሺህ ብር/ ለሎት 4፡- 15,000 ብር /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ለሎት 5፡ 15,000 ብር /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ለሎት 6፡- 150,000 ብር /አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ ለሎት 7፡- 15,000 ብር /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ለሎት 8፡- 15,000 ብር /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ለሎት 9፡ 20,000 ብር /ሃያ ሺህ ብር/ ለሎት 10፡ 50,000 ብር /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉበትን እቃ በራሳቸው ትራንስፖርት እስከ ኤጀንሲው እቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታውን ፋይናንስ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም ቴክኒክ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን ትክክለኛውን ቅጂ ለየብቻው በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ናሙና እንዲቀርብ ለተጠየቁት እቃዎች ከጨረታው መክፈቻ ቀደም አድርገው ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከተጠቀሰው ቀን ዘግይቶ የሚቀርብ ናሙና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

7. የጨረታው ፋይናንስ ሰነድ የሚከፈተው እና ግምገማ የሚካሄደው ከላይ ከተራ ቁጥር 1-7 የተመለከቱት ቴክኒካል መረጃዎች እና የእቃው ናሙናዎች በትክክል ተሞልቶ መቅረባቸው ሲረጋገጥ ነው፡፡

8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉትıዐ ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 6.30 እና ከቀኑ 7፡30 እስከ 1፡30 ሰዓት ድረስ ከጎላጎል ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ዋናው መስሪያ ቤት 13ኛ ፎቅ ላይ የግዥ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በመምጣት የማይመለስ 300 ብር/ ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

10ኤጀንሲው አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡

11 በለሎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይቻልም፡፡

12. ኤጀንሲው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ
ከጎላጎል ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ዋናው መስሪያ ቤት ህንፃ 13ኛ ፎቅ ወይም በስልክ ቁጥር 011 812 5085 ደውለው ያነጋግሩ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ