Addis Zemen (Nov 08, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በ2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የሚያስፈልጋቸው፡ የጽዳትዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ መስተንግዶ አገልግሎትና የሰራተኞች ካፌ አገልግሎት ግዥን አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታ መወዳደር የሚችሉ አቅራቢዎች፡–
1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የንግድ መለያ ቁጥር TIN
3. የዘመኑን ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉ እና ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን ድጋፍ 12. ደብዳቤ ከገቢዎች ማቅረብ ሚችሉ፤
4. የአቅራብነት ሰርትፍኬት ያላቸው /ከአቅራብነት ያልተወገዱ፤
5. ቫት የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት CPO በሚያቀርቡት ገንዘብ ዋጋ፡–
|
ሎት |
የዕቃ /አገልግሎት ዓይነት |
በመቶኛ |
የጨረታማስከበሪያ ብር መጠን |
|
1 |
አላቂ የቢሮ ዕቃዎች |
1% |
10,000.00 |
|
2 |
የፅዳት ዕቃዎች |
1% |
15,000.00 |
|
3 |
ቋሚ ዕቃዎች |
1% |
45,400.00 |
|
4 |
ደንብ ልብስ |
1% |
11,000.00 |
|
5 |
መስተንግዶ |
1% |
5,000.00 |
|
6 |
የካፌ አገልግሎት |
1% |
25,000.00 |
7.ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት አዲሱ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት እና እዛው ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
8. የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መሞላት ያለባቸው ክፍሎች በሙሉ በመሙላት በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና ማህተም በማሳረፍ በታሸገ ኤንቭሎፕ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋናውን እና ከላይ ከ1-6 የተጠቀሱትን ሰነዶች ኮፒ በአንድ ላይ ማሸግ፤ ኮፒዎቹንም ለየብቻ ማሸግ እና የቴክኒካል ሰነድ ወይም ናሙና ለማቅረብ ለማያስፈልግ ለብቻ በማሸግ በእያንዳንዱ ላይ ሙሉ አድራሻ በትክክል በመሙላት ሶስቱንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
10.የጨረታ ሰነዱ በሙሉ የማይመልስ አቅራቢ ከጨረታው ይሰረዛል፤
11.በጥቃቅንና አነስተኛ፤በአካል ጉዳተኞች ማህበር እና ነጋዴ ሴቶች ማህበራት የተደራጃቹ በራሳቹ ምርት ላይ ልዩ አስተያየት ስለሚደረግ፤ የጨረታ ሰነዱንም ያለ ክፍያ እንድትወስዱ አምራች መሆናቹን፤ የመልካም ስራ አፈጻጸም መረጃ፤ፈቃዳቹን ለሌላ ያላስተላለፋቹ መሆኑን የሚገልፅ መረጃ ካደራጃቹ አካል የድጋፍ ደብዳቤ በጽ/ቤት ኃላፊ ብቻ የተፈረመ እና የምትወዳደሩበት ሎት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን የተጠቀሰበትን ማቅረብ አለባችሁ፤
12.ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያውኑ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ 11ኛው ቀን ስራ ያለበት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፤
13.ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ 2 ቀን በፊት ለሁሉም ዕቃዎችናሙና ወይም ስፔስፍኬሽን ስለ ዕቃው በደንብ በሚገልጽ መልኩ ተዘጋጅቶ ማቅረብ መቻል አለባቸው፤ የናሙና መቀበያ ቅፅ በ2 ኮፒ አዘጋጅቶ የድርጅቱ ማህተም በማድረግ አብሮ ማቅረብ መቻል ያለባቸው ሲሆን፤ የሚቀርቡ ናሙናዎች ላይ ምንም ዓይነት ምልክትና ጽሑፍ መደረግ የለትም፤ ወይም ምልክት ማህተም/ ጽሁፍ የተደረገበት ናሙና ወይም የናሙና መያዣ እቃዎች በቀላሉ የሚቀደዱ ከሆኑ የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን፤
14. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ VAT ጨምሮ ያለ ስርዝ ድልዝ በትክክል መሞላት አለበት
15. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው ከሆነ ተቀባይነት የለውም፡፡
16. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ የጨረታ ውጤት ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በ8ኛው ቀን ውል መፈረም አለበት፤
17.ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻልም፤
18.መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– ከአውቶቢስ ተራ ወደ አጣና ተራ በሚወስደው መንገድ ሰፈረ ሰላም ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል ፊትለፊት 200 ሜትር ገባ ብሎ
በአ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 4 አስተዳደር አዲሱ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት የ ቢሮ ቁጥር 203፤
ስልክቁጥር፡– 011-279-3338
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት