Addis Zemen (Nov 08, 2026)
በድጋሚ የወጣ ዓለም አቀፍ — የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001 /2019
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት የማተሚያ ማሽኖችን ከቅድመ ህትመት እስከ ድህረ ህትመት ማለትም
- sheet fed offset press,
- folding machine,
- paper cutting machine,
- perfect binding machine,
- double saddle stitcher,
- laminating machine,
- heavy duty printer,
- Thermal ctp በዓለም አቀፍ የግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
1. የብቃት መስፈርቶች
- ለሀገር ውስጥ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
- የንግድ ምዝገባ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት
- የቫት ሰርተፍኬት
- በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበ
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል በዘመኑ የተሰጠ የግብር ክፍያ ማረጋገጫ ደብዳቤ (Tax Clearance)
ለውጭ ተጫራቾች ደግሞ፡-
- ህጋዊ እና የንግድ ፈቃድ ማረጋገጫዎች
- በተመዘገቡበት ሀገር ህጋዊ ኩባንያ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የንግድ ምዝገባ ሰነድ
- በተፈለገው የስራ ዘርፍ ለመሰማራት የሚያስችል የታደሰ የንግድ ፈቃድ
- ተመዘገበበት ሀገር ከሚመለከተው የታክስ ባለስልጣን የተሰጠ ህጋዊ የግብር ክፍያ ማረጋገጫ ሰነድ (Tax Clearance Certificate)
- Power of Attomey: የድርጅቱ ወኪል ወይም ህጋዊ ተወካይ ጨረታውን ለመፈረምና ለማስገባት የሚያስችለው የተፈረመና የታተመ የውክልና ሰነድ
- በኢፌዲሪ መንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበ
2. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond)
- መጠን፡ 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ወይንም በውጭ ሀገር መገበያያ ገንዘብ (የአሜሪካ ዶላር፣ የእንግሊዝ ፓውንድ፣ ወይም ዩሮ) በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ (Bank Guarantee) ወይምለጥቃቅንና አነስተኛ ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ በማያያዝ፡፡
- ማሳሰቢያ፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒክ ዋና ስነድ (Technical Original) ፖስታ ውስጥ ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
3. የሰነድ አቀራረብ እና ማቅረቢያ ደንቦች
- ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 45 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተጫራቾች የማይመለስ 100 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ሰነዶቹ በአንደኛ ፎቅ በሚገኘው አቅርቦት መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካል ዶክመንት (ዋና እና ቅጂ) እንዲሁም የሚወዳደሩበትን ዋጋ (ዋና እና ቅጂ) በሚል በጉልህ በሚታይ መልኩ በመጻፍ በአራት የተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ስርዝ ድልዝ ያለውና ያልተፈረመ እንዲሁም በጉልህ የማይታይ አጠራጣሪ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
4. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ መርሃ-ግብር
- የጨረታ መዝጊያ፡ ጨረታው በ46ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ
- የጨረታ መክፈቻ፡ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
- ማሳሰቢያ፡የተጫራቹ አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም፡ የጨረታ መክፈቻው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
5. የድርጅቱ መብቶች እና አድራሻ
- ድርጅታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ፡ አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት
- ኢሜይል (e-mail): procurement@press.et
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት