2merkato.com (Nov 09, 2026)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
አስራ ስድስት (16) የቆዳ ስፌት ማሽኖችን ለመገዛት ድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ዩዝ ኤንድ ካልቸራል ዲቨሎፕመንት ፋውንዴሽን (Youth and Cultural Development Foundation – YCDF) ወጣቶችን በተለያዩ የሙያና የተግባር ክህሎቶች እንዲሁም በሥራ ፈጠራ ዙሪያ በማሰልጠን፣ በማብቃትና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ወጣቶች የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩና በኢኮኖሚያዊ ሕይወታቸው ራሳቸውን እንዲችሉ የሚያግዝ ለትርፍ ያልተቋቋመ ሀገር በቀል ድርጅት ነው።
በአሁኑ ወቅት ማስተርካርድ ፋውንዴሽን (Mastercard Foundation) በኢማኑኤል የልማት ድርጅት(Emmanuel Development Association – EDA) በኩል “Windows of Hope” (የተስፋ መስኮቶች) የተሰኘውን ፕሮጀክት በዩዝ ኤንድ ካልቸራል ዲቨሎፕመንት ፋውንዴሽን በኩል እየተገበረ ይገኛል። ፕሮጀክቱ 275 ወጣቶችን በሥራ ፈጠራ፣ በሕይወት ክህሎት እና በቆዳ ስፌት ሙያ ሥልጠና በማብቃት የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ ለማገዝ ያለመ ነው።
የፕሮጀክቱን ዓላማ ለማሳካት YCDF አስራ ስድስት (16) የቆዳ ስፌት ማሽኖችን ለመግዛት ያቀደ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት ብቁ እና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች የታሸገ የጨረታ ሰነድ እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።
ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በድጋሚ የመጣ ሲሆን በማስታወቂያው የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ፍላጎት ያላቸው አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1. የማሽኖቹ ቴክኒካዊ መስፈርቶች
የሚቀርቡት የቆዳ ስፌት ማሽኖች ቢያንስ የሚከተሉትን ቴክኒካዊ መስፈርቶች ሟሟላት አለባቸው።
- የማሽኑ ዓይነት፡ ከባድ የሥራ ጫናን መቋቋም የሚችል የቆዳ ስፌት ማሽን (Heavy-Duty Walking-Foot Leather Sewing Machine)
- የመርፌ ዓይነት፡ DP × 17 (#18–23)
- የስፌት ሥርዓት፡ አንድ መርፌ እና ሁለት ክር (Single Needle, Two Thread System)
- የስፌት ርዝመት፡ ከፍተኛው 9 ሚሊ ሜትር
- የመንጠቆ ዓይነት፡ ድርብ አቅም ያለው መንጠቆ (Double-Capacity Hook)
- የማሽኑ የመሥሪያ ወለል መጠን፡ 477 × 178 ሚሊ ሜትር
- የኤሌክትሪክ ኃይል፡ 220–240V፣ 50Hz
- አብሮ የሚቀርቡ ዕቃዎች ፡ የማሽን ጠረጴዛ፣ በቀጥታ ከሞተር ጋር የተገናኘ የኃይል ማስተላለፊያ (Direct-Drive Motor)፣ ማቆሚያ እግር፣ የእግር መቆጣጠሪያ (Foot Pedal)፣ አስፈላጊ መለዋወጫዎች እና የአጠቃቀም መመሪያ መካተት አለባቸው።
- ዋስትና፡ ቢያንስ የ12 ወራት ዋስትና።
- ከሽያጭ በኋላ የሚሰጥ አገልግሎት፡ የመለዋወጫ ዕቃዎች አቅርቦት፣ የጥገና እና የቴክኒክ ድጋፍ አገልግሎት መኖር አለበት።
ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ማሽን የብራንድ ስም፣ ሞዴል፣ የተመረተበትን ሀገር እና ዝርዝር ቴክኒካዊ መግለጫ በግልጽ ማቅረብ አለባቸው።
2. የተጫራቾች ማቅረብ ያለባቸው ሰነዶች እና የዋጋ ዝርዝር
ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ከዋጋ ማቅረቢያቸው ጋር የሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ አለባቸው፦
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተ.እ.ታ (VAT) ምዝገባ ማረጋገጫ
- ወቅታዊ የግብር ክሊራንስ ማረጋገጫ
- የድርጅቱ መግለጫ (Company Profile)፣ በተለይም የስፌት ማሽኖችን ወይም ተመሳሳይ መሣሪያዎችን በማቅረብ ያለውን ተዛማጅ ልምድ የሚያሳይ።
- ለእያንዳንዱ ማሽን የአንዱን ዋጋ እና የአጠቃላይ የ16ቱን ማሽኖች ዋጋ ታክሶች ጨምሮ
- ከተጠየቁት ቴክኒካዊ መስፈርቶች ጋር መጣጣሙን የሚያሳይ የምርት ካታሎግ፣ የቴክኒክ መግለጫ ሰነድ ወይም ሌላ ተዛማጅ ማስረጃ።
3. የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ እና የመጨረሻ ቀን
ተጫራቾች የተሟላ የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማስገባት ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ ማቅረብ አለባቸው።
በፖስታው ላይ የሚከተለው ጽሑፍ በግልጽ መጻፍ አለበት፦
“አስራ ስድስት (16) የቆዳ ስፌት ማሽኖች አቅርቦት”
ተጫራቶች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ህዳር 10 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት በፊት ከታች በተገለጸው አድራሻ ማስገባት አለባቸው።
ተጫራቶች ጨረታው በወረቀት ሰነድ (Hard Copy) አድርገው በአካል YCDF ቢሮ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። ኢሜይል ጨምሮ በኤሌክትሮኒክስ መንገድ የሚላኩ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
4. የጨረታ ሰነዶች መክፈት
የጨረታ ሰነዶች በYCDF የጨረታ ኮሚቴ በድርጅቱ የግዥ አሠራርና ሥነ-ሥርዓት መሠረት ይከፈታሉ። በጨረታ መክፈቻው ወቅት የሚካሄዱ ሂደቶች በደቂቃ መዝገብ(minutes) በአግባቡ ይመዘገባሉ።
YCDF በድርጅቱ የግዥ ሥነ-ሥርዓት መሠረት ማንኛውንም ጨረታ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበውንም ተጫራች ጨምሮ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመቀበል ወይም የመሰረዝ መብቱን የጠበቀ ነው።
5. የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ አድራሻ
ዩዝ ኤንድ ካልቸራል ዲቨሎፕመንት ፋውንዴሽን/Youth and Cultural Development Foundation(YCDF)
አድራሻ፡ ጉርድ ሾላ፣ ከሴንቸሪ ሲቲ ሞል አጠገብ፣
ሴንፐር ህንፃ፣ ሁለተኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 201፣
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
ከጨረታው ጋር በተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ ወይም ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ተጫራቾች በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮችና ኢሜይሎች
መጠቀም ይችላሉ።
ስልክ፡ +251 911 412 214 / +251 988 043 116
ኢሜይል፡ addiswork.t@ycdfet.org / meronycdf@gmail.com
ተጫራቾች ከታች የሚገኘውን QR ኮድ ስካን በማድረግ ሙሉ የጨረታ ሰነዱን ማግኘንት ይችላሉ፡፡
አልያም፣ ተጫራቾች ሙሉ የጨረታ ሰነዱን ከታች ባለው የኢሜይል አድራሻ እስከ ህዳር 7 ቀን 2019 ዓ.ም. መጠየቅ ይችላሉ፦ meronycdf@gmail.com
Click the link to open the bid announcement