Addis Zemen (Nov 10, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የካ ቅጕርጫፍ ጽ/ቤት በ2019 በጀት የአንደኛ ዙር ግልፅ ጨረታ፣
- ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችን ፣
- ሎት 2 ህትመት
- ሎት 3. የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት 4 አነስተኛ የቢሮ መገልገያዎች እና
- ሎት 5 መኝታ ልብሶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
1. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ ንድፍ
2. በመስኩ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልጽ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ የተሰጠ ማስረጃ እና የግብር መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ።
3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ከወሰዱት የጨረታ ሰነድ ዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ውጪ በሌላ ሞልቶ ቢያቀርቡ ተቀባይነት አይኖረውም።
5. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
6. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ለመጡ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል እና ፋይናሽያል በተለያየ ፖስታ ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው፤ በ11ኛው ቀን እስከ አራት ሰአት ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው እለት ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፉ አዳራሽ ውስጥ የሚከፈት ሲሆን በኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
8. በጨረታው ለመሳተፍ ከሎት 1- 5 ላለው ለእያንዳንዱ ሎት 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማሲያዝ አለባቸው።
9. ዘግይተው የቀረቡ የመወዳደሪያ ሠነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
10.ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ የሚሆኑ ሲሆን ወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
11. በጨረታው ተወዳድሮ ያሸነፈውን እቃ በቅርጫፉ ጥራት /ቴክኒክ ኮሚቴው ጥራቱ ሲረጋገጥ ተጫራቹ በራሱ ትራንስፖርት ጭኖ በቅርጫፉ ንብረት ክፍል ማድረግ ይኖርበታል።
12. ተጫራቾች ለጨረታው ያቀረቡት ዋጋ የሚቆይበት ጊዜ ቢያንስ ለ6 ቀናት መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል ፡
13. ቅርጫፉ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ እንደአስፈላጊነቱ እስከ 20 በመቶ ለመቀነስ ወይም የሚገዛውን እቃ ወይም አገልግሎት ብዛት መጠን ለመጨመር መብት ይኖረዋል፡፡ በስብሰ
14 በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የካ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
15. ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ ወይም መረጃ ማግኘት ሲፈልጉ በስልክ ቁጥር 0116-68-47-97/0116- 66-81-73 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- አድራሻ ፡- ከማዕድን ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ ዬድ አቢሲኒያ ኢተርናሽናል ሆቴል አጠገብ
- በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት 01-16-6847-97
በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የካ ቅንርጫፍ ጽ/ቤት