በደቡብ ወሎ ዞን የሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግዥ ፋይ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት የቧንቧ መገጣጠሚያዎች፣ የንጽህና መጠቀሚያዎችን እና የጽህፈት መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በደቡብ ወሎ ዞን የሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግዥ ፋይ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት የቧንቧ መገጣጠሚያዎች፣ የንጽህና መጠቀሚያዎችን እና የጽህፈት መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Nov 09, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ወሎ ዞን የሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግዥ ፋይ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት የቧንቧ መገጣጠሚያዎች፣ የንጽህና መጠቀሚያዎችን እና የጽህፈት መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
  3.  የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  4. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱ ሲገዙ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ ድምር ብር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱ ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታዉ በ16ኛ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ይከፈታል፡፡ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ቀን ይከፈታል፡፡
  9. የንጽህና መጠበቂያና የጽህፈት መሳሪያ አሸናፊ የሚለየዉ በሎት ጠቅላላ ዋጋ ነዉ፡፡
  10. የቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎች አሸናፊ የሚለየዉ በተናጠል ዋጋ ነዉ፡፡
  11. ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ከጨረታዉ ዉድድር ማግለል የማይችል ሲሆን በጨረታ ሰነዱ የሰጠዉን ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም፡፡
  12. ጽ/ቤቱ እንደበጀቱ ሁኔታ በጨረታዉ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ብዛት መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል፡፡
  13. ሁሉም የሚቀርቡ ዕቃዎች ጥራታቸዉ የተጠበቀ መሆን አለበት፡፡
  14. አሸናፊዉ ድርጅት ዕቃዎቹን ሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ወጭ አጓጉዞ በማቅረብ ንብረቱን አስረክቦ ገንዘቡን ወጪ አድርጎ ይወስዳል፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  16. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 222 10 65 /033 222 04 83 ደዉሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *