Be'kur (Nov 09, 2026)
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሣሽ ደመላሽ አዳነ እና በአፈ/ተከሣሾች 1. አቶ እሱባለው አዲስ 2. አቶ አዳምጣቸው አዲስ መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ የተከሳሾች ንብረት የሆነው ቤት የ1ኛ አፈ/ተከሳሽ በቁጭ ከተማ 02 ቀበሌ አዋሣኙም በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ግዛቸው፣ በሰሜን አሰፋ ጀንበሬ እና በደቡብ መንገድ የሚገኘው ስፋቱ 240 ካ/ሜትር ቤት ህዳር 25 2019 ዓ/ም ከረፋዱ 3፡00 እስከ 6፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ በጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 1,570.840 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሰባ ሽህ ስምንት መቶ አርባ ብር) ይሸጣል፡፡ የ2ተኛ አፈ/ተከሳሽ በቁጭ ከተማ 01 ቀበሌ በአዋሳኙም በምሥራቅ ቢተው ይመር፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን ደሴ አባት እና በደቡብ አማረ ዘሩ ስፋቱ 200 ካ/ሜ ቤት በቀን ህዳር 25 2019 ዓ/ም ከረፋዱ 3፡00 እስከ 6፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ በጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 1,295,470 (አንድ ሚሊዩን ሁለት መቶ ዘጠና አምስት ሽህ አራት መቶ ሰባ ብር) በግልጽ ጨረታ ይሸጣል የጨረታ አሸናፊ ¼ ማስያዝ አለበት ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የቁጭ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት