Be'kur (Nov 09, 2026)
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሳሽ አቶ አዝመራው ዳኛው እና በአፈ/ተከሳሾች 1ኛ. እነ ይቻላል ምናየሁ፣2ኛ ወ/ሮ በላይነሽ ብዙየ 2ቱ ራሳቸው መካከል ስላለው የገንዘብ ክርክር ጉዳይ፤ በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 05 በሰሜን መንገድ፣ በደቡብ ሀብታሙ መኮነን፣ በምስራቅ መሰረት ቸኮል እንዲሁም በምእራብ ገረመው ታመነ መካከል ተዋስኖ የሚገኘው፤ በአፈ/ተከሳሽ በላይነሽ ብዙየ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የድርጅት ቤት በመነሻ ዋጋ 2‚896‚245 (ሁለት ሚሊዬን ስምንት መቶ ዘጠና ስድስት ሽህ ሁለት መቶ አርባ አምስት) ብር ይሸጣል፡፡ በመሆኑም የጨረታ ማስታወቂያው ከጥቅምት 30/2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 30/2019 ዓ.ም ድረስ ለ30 ቀናት በጋዜጣ ታትሞ ቆይቶ፤ ታሕሳስ 1/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ስለሚሸጥ፤ ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ኛውን በሲፒኦ አስይዛችሁ እንድትቀርቡ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍ/ቤት