Be'kur (Nov 09, 2026)
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሳሽ ከፍያለው አያሌው እና በአፈ/ተከሳሽ ጌትነት ዳኛው መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ፤ በግ/ቤት ከተማ ቀበሌ 02 በሰሜን ቴሌኮምኒኬሽን፣ በደቡብ መንገድ፣ በምስራቅ ግብርና ጽ/ቤት እንዲሁም በምእራብ ወንዴ ባያብል መካከል ተዋስኖ የሚገኝ የድርጅት ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 14‚225‚136 (አስራ አራት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃያ አምስት ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ ስድስት) ብር ይሸጣል፡፡ በመሆኑም የጨረታ ማስታወቂያው ለ30 ቀናት በጋዜጣ ታትሞ ቆይቶ፤ ታሕሳስ 1/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ስለሚሸጥ ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ኛውን በሲፒኦ አስይዛችሁ እንድትቀርቡ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍ/ቤት