የወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማ፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ ተገጣጣሚ የቢሮ ዕቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማ፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ ተገጣጣሚ የቢሮ ዕቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Be'kur (Nov 09, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መስሪያ ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል 

  • ሎት 1. የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  • ሎት 3. አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣
  • ሎት 4. የመኪና ጎማ፣
  • ሎት 5. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣
  • ሎት 6. ተገጣጣሚ የቢሮ ዕቃዎች እና
  • ሎት 7. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

 ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1.  በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ መለያ ቁጥር (ቲን) እና የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ከሚመለከተው የገቢ ተቋም የዘመኑን /የወቅቱን/ የታክስ ክሊራንስ መረጃ /ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የዋጋ መጠኑ ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ለመሆኑ የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4.  እያንዳንዱ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ወደ ጎን እና ወደ ታች ክፍት ሳይደረግ ሙሉ በሙሉ ተባዝቶ መቀመጥ አለበት፡፡ ይህ ሆኖ ካልተገኘ ግን ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን ወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1.5 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጽ/ቤቱ መሂ 1 በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. የመጫረቻ ሰነዱ ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ፣ ፍቀት፣ ፍሉድ እና ፓራፍ ቢደረግም ከውድድር ውጭ ይደርጋል፡፡
  8. አጠቃላይ የተጫራቾች ሰነድ ሙሉ በሙሉ ከተፈረመበትና በተጫራቹ ከተረጋገጠ በኋላ ፎቶ ኮፒ ተነስቶ ለብቻው ኮፒ በሚል ፖስታ ዋናውን እና የዋጋ ማቅረቢያ ከልዩ ልዩ ማስረጃዎች ጋር ኦርጅናል የዋጋ ማቅረቢያ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. መስሪያ ቤቱ ውል ከመፈረሙ በፊት የቀረበው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
  10. የቀረበው ዋጋ ከገቢያ ዋጋ 10 በመቶ በላይ ከሆነ እንደተጋነነ ዋጋ የሚቆጠር እና የቀረበው ዋጋ ከገቢያ ዋጋ 30 በመቶ በታች ከሆነ እንደተሰበረ ዋጋ የሚቆጠር ሲሆን የተሰበረ የጨረታ ዋጋ ከቀረበም ከመደበኛው 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በተጨማሪ፣ በእያንዳንዱ አንድ በመቶ የዋጋ ልዩነት 2 በመቶ በመጨመር በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ተጨማሪ ዋስትና የሚያሲይዝ ይሆናል፡፡
  11. የሒሳብ ማስተካከያው (የአርቲሜቲክ ውጤቱ) በጨረታ መክፈቻ ወቅት ከተነበበው ዋጋ ጋር ሲነፃፀር ከ3 በመቶ በላይ (ወደ ላይም ሆነ ወደ ታች) ልዩነት ካሳየ ተጫራቹ ከውድድሩ ውጭ ይደረጋል፡፡
  12. ለግምገማ የሚውለው የማወዳደሪያ ዋጋ 50 በመቶ ስልጣን በተሰጠው ተቋም ከተዘጋጀው የገበያ ጥናት አማካይ ዋጋ እና 50 በመቶ ደግሞ ከዝቅተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ከ1-3 ካሉት ተወዳዳሪዎች አማካይ መነሻ ዋጋ በመውሰድ የሁለቱ ድምር ውጤት መሠረት ለእቃው ዋጋ ግምገማ ይሆናል፡፡
  13. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከጥቅምት 30/2019 እስከ ህዳር 09/2019 ለተከታታይ 10 ቀናት ቆይቶ ህዳር 10/2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በገምጋሚ ኮሚቴው ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ወይም ዕሁድ እና ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  14. ስለሚቀርበው ዕቃ ወይም አገልግሎት ጥራት እና ደረጃውን የጠበቀ ለመሆኑ በሚመለከተው የጥራት ኮሚቴ የሚረጋገጥ ሆኖ ዕቃው መቅረብ ያለበት በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ሲሆን ማንኛውንም የመንግስት ግብር፣ ታክስ የመጓጓዣ፣ የጉልበት ዋጋ በአቅራቢው የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  15. የሚቀርበው ዕቃ ወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ይሆናል፡፡
  16. መ/ቤቱ ስለ ጨረታው የተሻለ አማራጭ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ስለሆነ በጨረታው አይገደድም፡፡
  17. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሎት ድምር ብቻ ይሆናል፡፡
  18. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 118 05 21 ቢሮ ቁጥር 06 በአካል በመገኘት ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት