በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 11, 2026)

 የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ

  •  የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው።
  2. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበትና ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. በአቅራቢዎች ዝርዝር ስለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘረውን እያንዳንዱን ዋጋ ሞልተው ፈርመውና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የኤሌክትሮኒክስ ፋይናንሽያል ኦሪጅናል አንድ ፎቶ ኮፒ እና ቴክኒካል ኦሪጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ ለብቻ ለብቻ እና በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ግ/ን/ አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀ ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን ንግድና ገበያ ልማት ግ/ን/አስ/ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ በመምጣት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ሰነድ መሸጫ ዋጋ 500 (አምስት መቶ) ብር፣ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (cpo) ለኤሌክትሮኒክስ 30,000 (ሰላሳ ሺ) ብር ከቴክኒካል ኦሪጅናል ዶክመንት ጋር አሽጋቹ ማቅረብ አለባችሁ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ወዲያውኑ ተጫራች(ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ነገር ግን በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆ በሚቀጥለው የስራ ቀን 5፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡00 ሰአት ይከፈታል።
  9. ተጫራቾች በተወዳደሩበት የዕቃ አይነት ያሸናፊነት ደብዳቤ እንዲደርሳቸው መስሪያ ቤት በመምጣት በ5 የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ጠቅላለ ዋጋ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ጋራንቲ በማስያዝ ከቢሮው ጋር ውል መግባት አለባቸው።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ሲሞሉ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ መሙያ መሆን አለበት አልያ ውድቅ ይደረጋል።
  11. በጨረታ ላይ የወጡ ዕቃዎችን በሙሉ ኦሪጅናልና ጥራቱን የጠበቀ መሆን ይኖርበታል።
  12. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር መስፈርቶችን ከጨረታ ሰነዱ መረዳት ይቻላል።
  13. ጨረታው አየር ላይ ጸንቶ የሚቆየው ለ 45 ቀናት ብቻ ነው።
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 145 9423/ 046 145 8944 ወይም 09 12 70 65 05/ 09 13 12 40 44

አድራሻ፡- ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ቡታጅራ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *