የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው ለመንገድ ጥገና እና ግንባታ ስራ አገልግሎት የሚዉል ሲሚንቶ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው ለመንገድ ጥገና እና ግንባታ ስራ አገልግሎት የሚዉል ሲሚንቶ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 13, 2026)

በድጋሚ የወጣ የሲሚንቶ ብሔራዊ ግልጽ

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 08/2019

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው ለመንገድ ጥገና እና ግንባታ ስራ አገልግሎት የሚዉል ሲሚንቶ ለመግዛት ይፈልጋል።

 ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ለዉድድር ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) ያላቸው፣
  3. ተጫራቾች የሚጠበቅባቸውን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  4. የግዥው መጠን ከብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. የሚገዙ የስሚንቶ ዝርዝር መግለጫ /specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፤
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመ/ቤቱ አካውንት ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 በመክፈል የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ05/03/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 15/03/2019 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል፤
  7. ማንኛውም ተጫራች የማጫረቻ ሰነዱን ማለትም ዋናና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በአንድ ኢንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ኢፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ05/03/2019 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ቀን 15/03/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
  8. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትና ሌሎች ማነኛዉንም ግብር እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋን ጨምሮ መሆን አለበት ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የስሚንቶ ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፣ ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ከሆነ 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊዮን ብር/ ብቻ ማስያዝ ይችላሉ፤
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በቀን 15/03/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 8፡30 ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል፤
  10. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  11. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና መህተም ማድረግ አለባቸው። በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርስ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
  12. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058-322-5155 /058-222-1107 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  13. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ባህር ዳር

ፖ.ሳ.ቁ 382

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *