የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት Supply, Delivery, Installation & Commissioning of CCTV Cameras በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት Supply, Delivery, Installation & Commissioning of CCTV Cameras በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 13, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ፍፋግ / ግጨ-017/2019

ተቋማችን  Supply, Delivery, Installation & Commissioning of CCTV Cameras ግዥ በግልጽ ጨረታ  አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት

የዕቃው አይነት

የጨረታ ዋስትና  ማስከበሪያ(CPO)

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

1

Supply, Delivery, Installation & Commissioning of CCTV Camera

100,000.00

 

ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00ሰዓት

ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት

  1.  ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ፣ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
  2. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ፍሊትናፋሲሊቲ ግዥ ክፍል በመምጣት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድባንክ አካውንት ቁጥር 1000068699332 በመክፈል ሶፍት ኮፒ በኢሜይል አድራሻቸው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. አድራሻ፡– ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋናው መስሪያ ቤት ኛ ፎቅ ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ከፍል ስልክ ቁጥር 011-156-01-48
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና — ETHIOPIAN ELECTRIC UTILITY-> በሚል መሆን ይኖርበታል፤
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን፣ሰዓት እና አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  6. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
  7. ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ  አገልግሎት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *