Addis Zemen (Nov 13, 2026)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 005/2019 ዓ.ም
ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ቤቶችን መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የዋና መስሪያ ቤት ሱቆች ኪራይ አገልግሎት፤
- ሎት 2 የቃሊቲ መናኸሪያ ቤቶች፤
- ሎት 3 የሸበሌ ማደያ፤
1. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር የስራ ቀናት ከሎት 1 እስከ ሎት 3 ለእያንዳንዱ ሎት 1000 በመከፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 በአካል በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
2. ከሎት 1 እስከ ሎት 3 ተጫራቾች በዘርፉ ንግድ ምዝገባና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆነ እና የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) ያለቸው፤ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ከሎት 1 እስከ ሎት 3 ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የሚያቀርቡትን የጨረታ ሠነድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ ዋና እና ኮፒ በአንድ ፖስታ በማዘጋጀትና በኢንቨሎፕ በማሸግ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ኃላፊነት በተሰጠው አካል ተፈርሞበት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
4. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 (ሃያ ሺ ብር) ሲፒኦ /Bid Bond ወይም በባንክ የተመሰከረለት በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻው ቀን የዕረፍት ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይከፈታል።
6. አገልግሎታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከሜክሲኮ ወደ ልደታ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ነው።
ለተጨማሪ መረጃ
ስልክ ቁጥር፡– 011-550-4564
ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት