በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለ2019 ዓ.ም ስራ ላይ የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለ2019 ዓ.ም ስራ ላይ የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 14, 2026)

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለ2019ዓ.ም ስራ ላይ የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  1. ድሮን ካሜራ
  2. ላፕቶፕ ኮምፒውተር
  3. ዴስክቶፕ ኮምፒውተር
  4. ፕሪንተር
  5. ፎቶ ኮፒ ማሽን
  6. ዲጅታል መቅረጸ ድምጽ
  7. ዋይረለስ ማይክ
  8. ፍላሽ ዲስክ
  9. ኤክስተርናል ሀርድ ዲስክ
  10. ዩፒኤስ በመሆኑ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ የታደሰ ንግድ ፈቃድ የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀትና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

2. ተጫራቾች የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

3. የዘመኑን ግብር የከፈሉና በመንግስት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሚየሰቀርቡት ዋጋ ላይ 2% ገንዘብ ለጨረታ ማስከበሪያ በመ/ቤቱ ስም የተዘጋጀ ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

5. መስሪያ ቤታችን የሚገዛቸው የዕቃ ዓይነቶች የሚገልፅ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታው ሰነድ ውስጥ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በዝርዝር የተዘጋጀ የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀኖች የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል በቢሮዋችን ግዢ /ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 05 ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

6. ተጫራቾች ካሸነፉ ለሚዋዋሉበት ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ሲጠበቅባቸው የሚያቀርቡትን ዕቃ በመስሪያ ቤቱ ዕቃ ግምጃ ቤት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ቫትን ጨምሮ በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ለየብቻ ከአንድ ኮፒ ጋር መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን በመጨረሻው ቀን ከቀኑ በ5፡30 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቱ በ6፡15 ላይ የሚከፈት ይሆናል። በጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመኖር የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።

8. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ሳምፕል ለሚያስፈልገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

9. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሆኖ ብዛቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው እንደ ሁኔታው የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10.ጨረታውን አስመልክቶ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 09 10 28 85 29 ወይም በ09 39 56 37 49 ደውሎ ማረጋገጥ የሚቻል መሆኑን እናስታውቃለን።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *