Addis Zemen (Nov 15, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ሠነድ ቁጥር፦ ልዲቁኮ – 09/2019
ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ሸራተን ወንበር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መወዳደር ይችላል።
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ባህር ዳር በግዥና ንብ/አስ/ቡድን የስራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 008 በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያው ቀን ድረስ መግዛት ይቻላል፡፡
3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8:30 ሰዓት ላይ ለመገኘት የቻሉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
4. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን፣ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በሲፒኦ ወይም እንደተጠየቀ ወዲያውኑ በሚከፈል የባንክ ጋራንቲ በፖስታ አሽገው እስከ ጨረታ መዝጊያው ቀንና ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 008 ማቅረብ ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
5. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 058-218-02-73 ሞባይል 09 18 08 55 89 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 058-218-05-50 በመላክ መጠየቅ ይቻላል።
ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮር ፖሬሽን ባህርዳር, ኢትዮጵያ