የባንጃ ወ/ ፍ/ቤት የ250 ካ.ሜ መኖሪያ ቤት የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል – test3.diretenders.com

የባንጃ ወ/ ፍ/ቤት የ250 ካ.ሜ መኖሪያ ቤት የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል


Be'kur (Nov 16, 2026)

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአፈ/ከሳሽ አቶ አንተነህ መኮነን እና በአፈ/ተከሳሽ ወ/ሮ ጸሀይነሽ ደመላሽ መካከል ስላለው የጋብቻ ክርክር ጉዳይ፤ በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 01 በሰሜን አበጀው አሊ፣ በደቡብ በላይ በየነ፣ በምስራቅ አሳዬ ታረቀኝ እንዲሁም በምእራብ መንገድ መካከል ተዋስኖ የሚገኘው፤ 250 ካ.ሜ የመኖሪያ ቤት ከ7 ዶርም ጋር በመነሻ ዋጋ 2‚428‚902.5 (ሁለት ሚሊዬን አራት መቶ ሃያ ስምንት ሽ ዘጠኝ መቶ ሁለት ብር ከአምስት ከ5/100 0/0) በጨረታ ስለሚሸጥ ከህዳር 7/2019 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 4/2019 ዓ.ም በተከታታይ ለ30 ቀናት በጋዜጣ ታትሞ ቆይቶ፤ ታህሳስ 8/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ድረስ ጨረታው ይካሄዳል፡፡ ተጫራቾች የመነሻ ዋጋውን ¼ኛውን ገንዘብ በሲፒኦ በባንክ በማስያዝ ቦታው ድረስ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ  አዝዟል፡፡

የባንጃ ወ/ ፍ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *