2merkato.com (Nov 16, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ጣምራ ለማህበራዊ ልማት ድርጅት ከተመሠረተበት 1990 ዓ.ም ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 29 ዓመታት በወጣቶች ልማት፣ በሥነ-ተዋልዶ ጤና፣ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሰውን ጾታዊ ጥቃት በመከላከል፣ በአካባቢ ጥበቃና የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭትና በሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች ዙሪያ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ክልሎችና በአዲስ አበባ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ለዚህም ተግባሩ ድርጅታችን ላበረከተው የማኅበረሰብ አቀፍ ጉልህ አስተዋኦ ከሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር፣ ከኦሮምያ ክልልና ከኢፊዲሪ መንግስት የሠርትፍኬት፣ የዋንጫ፣ የቦታና የመኪና ሽልማቶችን ያገኘ አንጋፋ ድርጅት ነው፡፡
ድርጅታችን ጣምራ ለማበራዊ ልማት ድርጅት በሲዳማ እና በኦሮሚያ ክልል እየተገበረ ለሚገኘው ICD ፕሮጀክት የሚውል Medium Size Potato Storage House በቀርከሃ የእንጨት አይነት የሚሰራ ቤት ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ጨረታውን መሳተፍ የምትፈልጉ እና ፈቃዱ ያላችሁ ድርጅቶች ፤ የዚህን ጨረታ ሃሳብ ዝርዝር የያዘውን ዶክመንት የማይመለስ 200 ብር በመክፈል፤ የጨረታ ሰነድ መግዛት እና ጨረታውን መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን ተጫራች ድርጅቶች ተወካይ መላክ የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
አድራሻ – አዲስ አበባ፣ቦሌ፣ወረዳ 07, ከሰአሊተ ምህረት ወደ ጃክሮስ በሚወስደው መንገድ፣ከመጀመሪያው የትራፊክ መብራት ቀጥሎ ከ አቢሲኒያ ባንክ ጀርባ
ለበለጠ መረጃ – +251 982024874 ይደውሉ፡፡
Deadline – ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም (November 19, 2026)