በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የመርሐቤቴ ወረዳ ፍ/ቤት የተለያዩ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የመርሐቤቴ ወረዳ ፍ/ቤት የተለያዩ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 18, 2026)

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የመርሐቤቴ ወረዳ ፍ/ቤት የግዥ ፋ/ን/አስ/ቡድን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ማለትም

  • ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ
  • ሎት 2 ጽዳት እቃ፣ 
  • ሎት 3.ኤሌክትሮኒክስ እቃ፣
  • ሎት 4 ልዩ ልዩ ህትመቶች 
  • ሎት 5. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና፣
  • ሎት 6. ደንብ ልብስ እንዲሁም ልዩ ልዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች በግልጽ ጨረታ ሀጋዊ የሆኑ ነጋዴዎችን አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል በመሆኑም

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN No) ያላቸው
  4. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
  5. ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው
  6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-5የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በግልፅ የሚነበብ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ፤በእያንዳንዱ ሰነድ ገፅ ላይ ከስራ ዘርፉ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ግልፅ የሚነበብ ማህተም መምታት አለባቸው::
  7. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification | ከጨረታ ሰነዱማግኜት ይችላሉ ::
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ 200 ብር /ሁለት መቶ ብር /በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ከቢሮ ቁጥር 09 መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ ለእቃው የሞሉትን ለፅህፈት መሳሪያ 4000ብር ለጽዳት እቃ 1000 ብር ለህትመት 2000ብር ለኤሌክትሮኒክስ እቃ 1500ብር ለደንብ ልብስ 2000 ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ / cpo / ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በውስጥ ገቢ ካርኒ አስገብቶ ኮፒውን ከሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው ::
  9. ተጫራቾች በቀረበው ዋጋ መሙያ ቦታ ላይ ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በመ/ወ/ፍ/ቤት የግዥ /ፋ/ን/አስ /ቡድን ቢሮ ቁጥር 09 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን እስከ 3፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ11ኛው ቀን 3፡01 ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚመጡ የጨረታ ሀሳቦች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት ማስታወቂያ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ 3፡30 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 09 ይከፈታል ፤የቫት ተመዝጋቢዎች ዝቅ ብለው ሲወዳደሩ ሰነዳቸው የተሟላ መሆን አለበት፡፡
  11. የጨረታው መክፈቻ በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል ::በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው :
  13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 09 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0910 473 819 ፤ 011 13 20 004 በመደወል መረጃውን ማግኜት ይችላሉ፡፡
  14. በማንኛውም ግዥ ከብር 20000(ሃያ ሺህ ብር) በላይ ለአገልግሎት ከብር 10000ብር (አስር ሺህ ብር ) በላይ የቅድመ ግብር ታክስ 3% ሶስት ፐርሰንት ተቀንሶ ለመንግስት ይከፈላል፡፡
  15. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን አድራሻ እና የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ መምታት አለባቸው፡፡
  16. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ ፤ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ይወረሳል፤ በመንግስት ጨረታ ላይ ለሁለት ዓመት እንዳይወዳደሩ ይደረጋል፡፡
  17. ስርዝ ድልዝ ፤ፍቀትያለው ፍሉድ የነካው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፤ በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  18. የጨረታ አሸናፊዎች እቃውን ፍ/ቤቱ በሚፈልገው ቦታ ቢሮ ቁጥር 09 ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው::
  19. ጨረታው ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ራሳቸውን ማግለል አይችሉም ፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የመርሐቤቴ ወረዳ ፍ/ቤት