በአ.ብ.ክ.መ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአ.ብ.ክ.መ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 18, 2026)

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአ.ብ.ክ.መ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶችን ማለትም፡–

  • ሎት 1 ፅህፈት መሳሪያ
  • ሎት 2 ህትመት
  • ሎት 3 የፅዳት እቃዎች
  • ሎት 4 አላቂ ቋሚ የቢሮ እቃዎች
  • ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  • ሎት 6፦ መስተንግዶ
  • ሎት፦ 7 ደንብ ልብስ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በቀን 09/03/2016 ዓ.ም የወጣውን ጨረታ በማየት ሰነፍን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1) አግባብ ባለው የመንግስት ተቋም የተሰጠ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የንግድ ምዝገባ ሰርትፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፤

2) ተወዳዳሪዎች በአበር ዓመቱ ተገቢውን የታከስና ግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚሳይ የታከስ ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣

3) ግዥው የተጨማሪ እሴት ታክስ የማይመለከተው ካልሆነ በስተቀር የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

4) የግዥ መጠኑ ከብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ/ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

5) ተጫራቹ የተሰጠውን የጨረታ ቅጽ በአግባቡ መሙላት የሚችሉ፤

6) በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 ላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት ተራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ከተራ ቁጥር 1-4 ላይ የተጠቀሱትን ኦርጅናል ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው።

7) ተጫራቶች ከሎት 1-7 ላሉት ለእያንዳንዱ የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ብቻ የእቃውን ጠቅላላ ግዥ ግምታዊ ዋጋ 2% ብር 8500 (ስምንት ሺህ አምስት መቶ ብር) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

8) ከተጫራቶች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታ ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኃላ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ቀናት ጸንቶ ይቆያል።

9) ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 09/03/2019 ዓ.ም አንስቶ ለተከታታይ 10 ቀናት በደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍቤት ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 06 ዘወትር በስራ ሰዓት 11፡30 ድረስ መውሰድ ይችላሉ።

10) ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያየ ፖስታ በማሸግ በደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት በሚገኝበት ከመነሀሪያ ገባ ብሎ ከኢትዩጰያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ደሴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከፍ ብሎ በሚገኘው ቢሮችን በግዥ ፋን አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ማስገባት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 09/03/2019 እስከ 18/03/2019 ዓ.ም 30 ድረስ መውሰድ ይችላሉ። የጨረታ ሳጥኑ በቀን 21/03/2019 ዓ.ም ከጧቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል። ይሁን እንጂ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል ከሆነና የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው የመክፈቻ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

11) አስፈላጊ ለሆኑ እቃዎች ፍርድ ቤቱ ሳምፕል የሚያቀርብ በሆኑ ሳምፕሉን በጥንቃቄ በማየት እቃዎችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

12) የጨረታ ውድድር የሚካሄደው በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም ያልተሞላ አይተም ከተገኘ ተጫራቶች ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ።

13) ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልፅ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ጨረታውን ካወጣው መስሪያ ቤት ጋር ከጨረታ መክፈቻ ቀን 5 (አምስት) ቀን በፊት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 311 1010 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

14) የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መደረግ ይኖርበታል። ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል።

15) ጨረታውን ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ጊዜ በኃላ ለ45 ቀናት ይሆናል።

16) ጨረታውን ለማዛባት የሞስከሩ ተጫራቶች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆንና ለወደፊቱም በመስሪያ ቤቱ ግዥ የማይሳተፍ እና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወረስ ይሆናል።

17) ግዥ ፈጻሚው አካል ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊው ተጫራች በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ እስከ 20 (ሀያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።

18) የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን በደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤት ንብረት ከፍል በራሱ ወጭ ማቅረብ ይጠበቅበታል።

19) መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መበቱ ያለው መሆኑን ይህ ሲባለ ጨረታውን በመሰረዙ ተጫራቶች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መስሪያ ቤቱ ሀላፊነት የማይወስድ መሆኑን እናሳወቃለን።

በአ.ብ.ከመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት