ኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር የተሸከርካሪ መለዋወጫ ለተሽ/ ሞደል-VOLVO Bus- B11B-Via- go/1050/2019) እና ጀነሬተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር የተሸከርካሪ መለዋወጫ ለተሽ/ ሞደል-VOLVO Bus- B11B-Via- go/1050/2019) እና ጀነሬተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 18, 2026)

በድጋሜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: OIT/N/Bid-02/2019

ኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር የተሸከርካሪ መለዋወጫ ለተሽ/ ሞደል-VOLVO Bus- B11B-Via- go/1050/2019) ና ጀነሬተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ ገዝታችዉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፡–

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳድሩ ተጋብዛችኋል።

1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለዉና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ።

2. የግብር መለያ ቁጥር (TIN) ያለዉና የቫት (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ።

3. ለጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 1% ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO/un Conditional Bank Guarante) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ የምችሉ።

4. ተጫራቾች የጨረታዉን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጋዜጣዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 14 (አሥራ አራት) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) ከፍለዉ ከኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት አ.ማ መካኒሣ በሚገኘዉ ኤስ–ሳራ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ከግዢ ክፍል መዉሰድ ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የዕቃዎቹን የዋጋ ዝርዝር መግለጫ ሰነድ በማዘጋጀት ዋጋዉን ከነተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) በመሙላት ስማቸዉን፣ፊርማቸዉንና አድራሻቸዉን በማስፈር ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንታቸዉን ኦሪጅናልና ኮፒዉን በተለያየ ካኪ ፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በ15ኛዉ ቀን እስከ ጧዋቱ 4፡00 ሰዓት በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታዉ የሚከፈትበት 15ኛዉ ቀን እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ ጨረታዉ የሚከፈተዉ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ይሆናል።

7. የጨረታዉ መዝጊያና መክፈቻ በ15ኛዉ ቀን ከጧዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በዚሁ ቀን 4:30 ላይ መከኒሣ በሚገኘዉ በድርጅቱ ዋና መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ግዢ ክፍል በይፋ ይከፈታል:: ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይሳተፉም የጨረታዉን መክፈት አያስተጓጉልም።

8. ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ የቀረበዉን የመወዳደሪያ ሀሳብ መቀየር ወይም ማሻሻል ወይም ከጨረታዉ መዉጣት አይቻልም።

9. አሸናፊ ተጫራቾች የጨረታዉ ዉጤት ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ዉስጥ ከዉል ሰጪዉ ጋራ ተስማምቶ መፈረም ይኖርባቸዋል።

10. አሸናፊ ተጫራች በሚደረገዉ ዉል መሰረት፣የሚያቀርቡት የተሽከርካሪ መለዋወጫና ጀነሬተር በተጠየቀው መሥፈርት በራሱ ትራንስፖርት ገላን በሚገኘዉ በድርጅቱ ነዳጅ ማደያ ዉስጥ ለንብረት ክፍል ገቢ የሚያደርግና የመለዋወጫዎች ብዛት ሊጨመርም ሊቀነስም ይችላል።

11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

ለበለጠ መረጃ፡ ስልክ ቁጥር 0974 320 682

ኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት አ.ማ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *